top of page

ግንቦት 13 2017 - ብሔራዊ ባንክ ስድስተኛውን የውጭ ምንዛሪ ጨረታ አውጥቷል

  • sheger1021fm
  • 10 minutes ago
  • 1 min read

ባንኩ በየሁለት ሳምንቱ እያወጣ ባለው የውጭ ምንዛሪ ጨረታ ነገ ይካሄዳል የተባለው ለ6ኛ ጊዜ ነው፡፡


በዚህም 50 ሚሊዮን ዶላር ለባንኮች አቀርባለሁ ብሏል፡፡


በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ባንኮች ነገ ከማለዳ 4 ሰዓት እስከ 6 ሰዓት ጨረታ ማስገባት እንዳለባቸውም ብሔራዊ ባንክ አሳስቧል፡፡


የውጭ ምንዛሪ አስተዳደር ፖሊሲ ላይ ለውጥ ተደርጎ ገበያ መር ይሁን ከተባለ በኋላ ብሔራዊ ባንክ እስካሁን 415 ሚሊዮን ዶላር በጨረታ ለባንኮች ሰጥቷል፡፡


ከሁለት ሳምንት በፊት በተካሄደው ጨረታ 60 ሚሊዮን ዶላር ቀርቦ 26 ባንኮች መሳተፋቸው ይታወሳል፡፡


በወቅቱም አንድ ዶላር በአማካይ 131.4 ብር መሸጡ አይዘነጋም፡፡


ለ6ኛ ጊዜ ለወጣው ጨረታ ከቀረበው 50 ሚሊዮን ዶላር ጋር ብሔራዊ ባንክ በጨረታ ለባንኮች ያቀረበውን 455 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page