ግንቦት 13 2017 - በኢትየጰያ የኤሌክትሪክ መኪኖች በየጎዳናው ላይ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡
- sheger1021fm
- 6 hours ago
- 1 min read
በኢትየጰያ የኤሌክትሪክ መኪኖች በየጎዳናው ላይ ማየት የተለመደ ሆኗል፡፡
መንግስትም በአስር ዓመታት ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሸከርካሪዎችን 500,000 ለማድረስ ዘርፉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም ይናገራል፡፡
የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እና በዘርፉ ለሚሰማሩ ተቋማት የተለያዩ የፖሊሲ ማበረታቻዎች እየተሰጠ መሆኑን ተከትሎ አምራቾች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው እንዲሰሩ መንገድ ከፍቷል ተብሏል፡፡
ከነዚህም መካከል ከቀናት በፊት የቻይናው ጂኤሲ #GAC ግሩፕ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን መሸጫ የንግድ ማዕከል ከፍቷል፡፡
በሂደትም ተሸከርካሪዎቹን በኢትዮጵያ የማምረት ውጥን እንዳለው የተነገረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የመኪና ምርቶችን ለኢትዮጵያ ገበያ ማቅረብ መጀመሩን ተናግሯል፡፡
በተጨማሪም የቻይናው ጓንዧ አውቶሞቢል ኩባንያ GAC ለአለም ገበያ ከሚያቀርባቸው ምርቶች አንዱ የሆነውን ˝GAC Aion˝ የተሰኘ ኤሌክትሪክ መኪና ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ ገበያ አስተዋውቋል፡፡
የሽያጭ፣ የጥገና እና የመለዋወጫ አገልግሎቶችን ይሰጣል የተባለው ይህ ድርጅት በሂደት ግን የኤሌክትሪክ መኪኖቹን በኢትዮጵያ ለማምረት እቅድ መያዙ ተነግሮለታል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…....
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN