ግንቦት 12 2017 የከተማ መሬት ይዞታና የመሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ
- sheger1021fm
- May 20
- 1 min read
የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 30ኛ መደበኛ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።
በዚህም ምክር ቤቱ በከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የቀረበለት የከተማ መሬት ይዞታና የመሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ፤ የከተማ መሬት ይዞታና የመሬት ነክ ንብረት ምዝገባ ረቂቅ አዋጅን በ2 ተቃውሞ በ3 ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አፅድቋል።
አዋጁ የከተማ መሬት አያያዝ ወጥነት ባለው መልኩ በማደራጀት በመላው የሃገሪቱ ከተሞች ያሉ የመሬት ይዞታዎችን መመዝገብ አስፈላጊ በመሆኑ የተሰናዳ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡
በመሆኑ ወደ ተግባር ሲገባ የመሬት አስተዳደር ስርዓትን ያቀለጥፋል፤ ህገ ወጥ የመሬት ወረራን፤ ብልሹ አሰራርንና ኢ-ፍትሃዊነትን ለማስቀረት ይረዳል ተብሎም ታምኖበታል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://shorturl.at/21bFN
Comments