ግንቦት 12 2017 - ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሃገራት በመጭው የክረምት ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተተነበየ
- sheger1021fm
- May 20
- 1 min read
ኢትዮጵያን ጨምሮ በምስራቅ አፍሪካ ሃገራት በመጭው የክረምት ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል ተተነበየ፡፡
መረጃውን ያወጣው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) የአየር ጠባይ ትንበያ ትግበራ ማዕከል ከፍተኛ የተባለው ዝናብ የመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ ሊያስከትል ስለሚችል ሃገራት የቅድመ ጥንቃቄ ስራ እንዲከወኑ አሳስቧል፡፡
ማዕከሉ ይህን ያለው 70ኛውን የምስራቅ አፍሪካ የአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንተና እና ትንበያ ፎረም በአካሄደበት ወቅት ነው።
በፎረሙም የዘንድሮው የክረምት ወቅት በተለይ በደቡብ ምዕራብ እና በሰሜናዊ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል በአብዛኛው የዝናብ መጠን ከመደበኛው በላይ መሆኑን ትንበያው ያመላክታል ተብሏል።
በመጪው የክረምት ወራት የሚኖረው የአየር ሁኔታ ከአሉታዊ ውጤቱ በስተጀርባ አውንታዊ ሚናም ሊኖረው እንደሚችልም ተጠቅሷል።
ለአብነትም ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች ግድቦችም በተሎ እንዲሞሉ ያስችላል ተብሏል።
Yorumlar