top of page

‘’የተሽከርካሪ አረቦን ክፍያ ጨመረ ስንል የአረቦን ተመኑ ጨምሯል ማለት አይደለም’’

  • 23 hours ago
  • 1 min read

የሰኔ 17/2018


አንድ ተሽከርካሪ ሊያጋጥመው ለሚችለው አደጋ ወይም ጉዳት የንብረቱ ባለቤት በመረጠው የኢንሹራንስ ኩባንያ የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ወይም መድን አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናል፡፡


የተሽከርካሪው ወቅታዊ ዋጋ፣ የተሽከርካሪው ዕድሜና ዓይነት፣ አገልግሎቱ እና የአደጋ ታሪኩን በማየት የኢንሹራንስ ኩባንያዎችም ለአንድ ተሸከርካሪ የሚጠየቀውን የአረቦን መጠንን ይተምናሉ፡፡


ነገር ግን የተሽከርካሪ አረቦን ክፍያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ክፍያው እየጨመረ ነው ሲሉ የመኪና ባለቤቶች ቅሬታ ሲያቀርቡ ይሰማል፡፡



የአረቦን ክፍያ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጨመረ ስንል የአረቦን ተመኑ ጨምሯል ማለት አይደለም ያሉት በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው የቡና ኢንሹራንስ አክሲዮን ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳኛቸው መሐሪ ነገር ግን ንብረቱ በገበያው ላይ የሚያሳያው የዋጋ መናር ነው ባለቤቱ በዓመት የሚከፍለውን የብር መተን የሚጨምርበት ብለዋል፡፡


ይህ ማለት አንድ የመኪና ባለቤት የኢንሹራንስ ተቋማት በመሄድ የተሽከርካሪ አረቦን ሲገባ ድርጅቱ ንብረቱ ያለበት የገበያ ዋጋ፣ ይዞታው እና ሌሎች መመዘኛዎችን በማስቀመጥ የአረቦን ተመን ያስቀምጣል፤ በዚያ በተቀመጠው ተመን መሰረት ባለቤቱ ክፍያን ይፈፅማል፡፡


ነገር ግን ባለቤቱ መጀመሪያ ሲከፍለው ከነበረው ክፍያ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ከመጣ የአረቦን ተመኑ ጨምሮ ሳይሆን በዚያን ጊዜ የነበረው የንብረት ዋጋ በመናሩ ምክንያት ነው ሲሉ ያስረዳሉ፡፡


በዚህም አሁን ላይ ተሽከርካሪው ያለው የገበያ ዋጋ ከአረቦን ከተመኑ ጋር ሲባዛ ክፍያውም በዚያው ልክ ስለሚጨምር እንጅ የአረቦን ተመኑ በየጊዜው ከፍ ስለሚል አይደለም ሲሉ ያስረዳሉ፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….

ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…








Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page