top of page

የጤና ስርዓቱን ለመደገፍ የ1.466 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈረመ።

  • sheger1021fm
  • 3 minutes ago
  • 1 min read

ታህሳስ 14/2018


የጤና ስርዓቱን ለመደገፍ የ1.466 ቢሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈረመ።


ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የጤና ሚኒስሯ መቅደስ ዳባ(ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቭን ማሲንጋ ፈርመውታል።


በስምምነቱ መሰረት በ5 ዓመት ውስጥ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጤና ስርዓት መደገፊያ የሚውል 1.016 ቢሊዮን ዶላር የምትሰጥ ሲሆን ኢትዮጵያ ደግሞ 450 ሚሊዮን ዶላር ትበጅታለች ተብሏል።


የሚተገበረውም እ.አ.አ ከ2026 እስከ 2030 መሆኑ ተነግሯል።


ree

ኤችአይቪ ኤድስ፣ ወባ፣ ቲቢ፣ የእናቶችና ህፃናት ጤና እንዲሁም ወረርሽኝ መከላከል እና መቆጣጠር በ1.466 ቢሊዮን ዶላሩ ከሚሰሩ ስራዎች መካከል መሆናቸው ተጠቅሷል።


አሜሪካ ባለፉት 20 ዓመታት በኢትዮጵያ የጤና ስርዓት መደገፊያ የሚሆን ከ5 ቢሊዮን ዶላር በላይ መስጠቷን በፊርማ ስነስርዓቱ ወቅት ተነግሯል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page