top of page

የካቲት 20፣2016 - ገንዘብ ነክ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን እና ተቋማትን እየመዘነ መረጃ የሚሰጥ አገልግሎት ሊጀመር ነው

በኢትዮጵያ ገንዘብ ነክ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ የሚሳተፉ ግለሰቦችን እና ተቋማትን እየመዘነ መረጃ የሚሰጥ አገልግሎት ሊጀመር ነው።


አገልግሎቱ በተለይም በድርሻ ገበያ ውስጥ የሚሳተፉ ግለሰቦች እና ተቋማት ትክክለኛ አቅም እንዲታወቅ ያደርጋል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት በዚሁ አገልግሎት ምንነት እና ጠቀሜታው ላይ ያተኮረ ውይይት አካሂዷል።


አገልግሎቱ የካፒታል ገበያን ጨምሮ በተለያዩ ገንዘብ ነክ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ስለሚሳተፉ ግለሰቦችና ተቋማት ምዘና ተደርጎ ውጤት የሚሰጥበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡


የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዝደንት ወይዘሮ መሰንበት ሸንቁጤ ‘’አገልግሎቱ ከገንዘብ ተቋማት ብድር ስለሚጠይቁ ግለሰቦች መረጃ የሚገኝበት ነው’’ ብለውናል።


ድርሻ ስለሚሸጡ ግለሰቦች እና ተቋማት በቂ መረጃ በመስጠት ሰዎችን ካልተገባ ጉዳት ማዳን የሚያስችል አገልግሎት እንደሆነም ወይዘሮ መሰንበት ተናግረዋል፡፡


በተለያዩ ንግዶች ውስጥ የሚገኙ ተቋማት እና ግለሰቦች የገንዘብ አቅማቸውን ማሳደግ ቢፈልጉ፤ ሰዎች አምነዋቸው ድርሻ እንዲገዙ ዋስትና የሚሰጥ አገልግሎት እንደሆነ በመድረኩ ላይ ለውይይት የሚሆን የመነሻ ሃሳብ ያቀረቡት የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አስፋው አለሙ ነግረውናል።


የብድር አቅም ግመታ አገልግሎት(Credit Rating Service) በአጠቃላይ ገንዘብ ነክ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ፍጥነት፣ ቅልጥፍና፣ ግልፅነት እና ተአማኒነት እንዲረጋገጡ ያስችላል ተብሏል።



ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



bottom of page