top of page

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የግብርና ምርቶች በእሴት ጭመራ እና የማምረቻ ዋጋ መቀነስ ካልተቻለ ተወዳዳሪ እንዳንሆን ሊያደርገን ይችላል ሲሉ አግሮ ኢኮኖሚስት አስጠነቀቁ፡፡

  • 1 hour ago
  • 2 min read

ሚያዝያ 28/2018


የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የግብርና ምርቶች በእሴት ጭመራ እና የማምረቻ ዋጋ መቀነስ ካልተቻለ ተወዳዳሪ እንዳንሆን ሊያደርገን ይችላል ሲሉ አግሮ ኢኮኖሚስት አስጠነቀቁ፡፡


የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የገቢያ አቅሙ በባለሙያዎች ሲመዘን 1.4 ቢሊዮን ህዝብን ታሳቢ ያደረገ ሲሆን 3 ትሪሊዮን ዶላር በአህጉሪቱ ውስጥ እንዲዘዋወር ያደርጋል፡፡


አፍሪካዊያን በንግዱ ስርዓታቸው እሴት መጨመር ላይ ትኩረት አድርገው የማይሰሩ ከሆነ ዋንኛው የዚህ ነፃ ንግድ ቀጠናው ፈታኝ ችግር ይህ ሊሆን ይችላል ተብሏል፡፡


ታደለ ማሞ(ዶ/ር) አግሮ ኢኮኖሚስት ሲሆኑ በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የግብርና ኢኮኖሚ ምርምር ዳይሬክተር ናቸው፡፡ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ለኢትዮጵያ ግብርና እድልም ስጋትም ይዞ ይመጣል ይላሉ፡፡


ምርቶችን በትክክል ካመረትንና በስፋት ከሰራን በአነስተኛ ወጪ ለምርቶቻችን ገበያ ማግኘት እንችላለን ብለዋል፡፡



በነፃ ገበያው የታሪፍ ቅናሽ ይኖረዋል ለገበያ ምርቶች ስናቀርብ በተሸከርካሪ ወደ አንዳአንድ ሀገራት በአንድ ቀን የማድረስ እድል ይኖራል እነዚህ ሁሉ ጥሩ እድሎች ይዘውልን ይመጣሉ ሲሉም ነግረውናል፡፡


ይህ መሆኑ ደግሞ በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለው የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እንዲጨምርና የአህጉሪቱ ባለሃብቶች አፍሪካ ውስጥ የበለጠ እንዲያመርቱ ውጤታማ እንዲሆኑ ሊያደርግ ይችላል በማለት ያስረዳሉ፡፡


ለኢትዮጵያ ይህ የንግድ ትስስር ስጋቶች ሊኖሩን እንደሚችል ይናገራሉ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው የማምረቻ ዋጋ ከፍተኛ ነው የሚሉት ዶክተር ታደለ ማሞ የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን ከሌሎች ጋር ሲወዳደር ገና ብዙ ይቀረናል ብለዋል፡፡


በዚህ ምክንያት የሀገር ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶች የእኛን ምርቶች እንዳይውጣቸው ስጋት አለ ሲሉም ጠቅሰዋል፡፡


ኢትዮጵ ከአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና ገበያ ተጠቃሚ ለመሆን የመሰረተ ልማት ስራው ላይ መበርታት አለባት ይላሉ አግሮ ኢኮኖሚስቱ ዶክተር ታደለ ማሞ፡፡


ከዚህ ባለፈም እሴት መጨመሩ ላይ ከወዲሁ በርትተን መስራት አለብን ያሉ ሲሆን ኢትዮጵ ውስጥ በምርት ላይ እየደባለቁ የመሸጡ አባዜ ወደ አፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠናው ነጋዴው ይዞ እንዳይመጣ በጥራት ላይ ብርቱ ስራ መሰራት አለበትም ብለዋል፡፡


ኢትዮጵ በግብርናው ዘርፍ የበለጠ ተወዳዳሪ ለመሆን ከፈለገች ከሌሎች ሀገራት የበለጠ ምን ማምረት እንዳለባት በመለየት በዚያ ምርት ላይ አተኩሮ መስራቱ ሊበረታታ ይገባል ሲሉም መክረዋል፡፡


ምርቱ ከሀገር ከመውጣቱ በፊት በቂ የጥራት ቁጥጥር መደረግ አለበት ለዚህ ይረዳ ዘንድም የጥራት መቆጣጠር አሰራሩን ማጠናከር ይገባልም ተብሏል፡፡


ሙሉውን ለማድመጥ…


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page