top of page

የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ያደረኩት የዕርድ ክፍሎች ማስፋፊያ ለፋሲካ በዓል ካቀድኩት በላይ ዕርድ እንዳከናውን አስችለውኛል አለ፡፡

  • 6 days ago
  • 1 min read

ሚያዝያ 5/2018


የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት የጨመርኳቸው አስር አዳዲስ ተሽከርካሪዎች እና ያደረኩት የዕርድ ክፍሎች ማስፋፊያ ለፋሲካ በዓል ካቀድኩት በላይ ዕርድ እንዳከናውን አስችለውኛል አለ፡፡


ድርጅቱ ለበዓሉ ከ4,500 በላይ እንስሳትን ዕርድ በማከናወን ስጋውን ለህብረተሰቡ እንዳቀረበ ነግሮናል።


የህገ ወጥ ዕርድ ጉዳይ ግን አሁንም ፈተና ነው ብሏል።


የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለፋሲካ በዓል ካቀደው በላይ የእንስሳት ዕርድ ማከናወኑን ተናገረ፡፡


ከአራት ሺህ በላይ እንስሳትን ዕርድ በማከናወን ስጋውን ለህብረተሰቡ ለማቅረብ አቅዶ እንደነበር ከድርጅቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አታክልቲ ገብረሚካኤል ሠምተናል።


ለበዓሉ ከአራት ሺህ አምስት መቶ በላይ እንስሳት ዕርድ በማከናወን ስጋውን ለህብረተሱ አቅርበናል ብለዋል።


ከተከናወነው ዕርድ ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዘው በሬ እንደሆነም አቶ አታክልቲ ነግረውናል።


ድርጅቱ ንጽህናው የተጠበቀ የዕርድ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን ስርጭት ላይ ሲቀርቡ የነበሩ ቅሬታዎችን ለመፍታትም በልዩ ትኩረት ሲሰራ እንደቆየ ሃላፊው ተናግረዋል።


ስርጭቱ ላይ ሲቀርብ የነበረውን ቅሬታ ለመፍታት በነበሩት ላይ አስር ዘመናዊ መኪኖችን በመጨመር አገልግሎት ስንሰጥ ነበር ብለዋል።


ጠባብ በነበሩ የእርድ ክፍሎች ላይ ማስፋፊያ በማድረግም የተሻለ አገልግሎት መቅረቡን ጠቅሰዋል።


ህገ ወጥ ዕርድ በስራው ላይ ተፅዕኖ እንደፈጠረበት ድርጅቱ በተደጋጋሚ ሲናገር ቆይቷል።


አሁንስ የተታየ መሻሻል አለ ወይ በሚል የጠየቅናቸው አቶ አታክልቲ ይሄ ነው የሚባል ለውጥ አልመጣም ሲሉ ነግረውናል፡፡


በቄራዎች ድርጅት የሚከናወን ዕርድ በብዙ ምክንያቶች ተመራጭ ነው የሚሉት አቶ አታክልቲ አንዱ ንጽህና እንደሆነ ጠቅሰዋል።


በዋጋም በኩል በአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ለሚከናወን ዕርድ የሚጠየቀው ክፍያ አነስተኛ እንደሆነ አመልክተዋል።


ህብረተሰቡም ይህንኑ ተረድቶ ዕርድ በቄራ እንዲከናወንለት ማድረግ እንዳለበት ጠቁመዋል።


በአዲስ አበባ የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ስር የሚገኘው የቄራዎች ድርጅት፣ የአገልግሎት ጥራቱን ይበልጥ ለማሻሻል እና

ተገልጋይን ማዕከል ያደረገ አገልግሎት ለመስጠት ወደፊትም በትኩረት እንደሚሰራ ተናግሯል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..

ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page