top of page

የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ ሀገሮች ተመድበው ሲሰሩ የቆዩ 29 የሀገሪቱን አምባሳደሮች ወደ አገር ቤት አስጠሯቸው፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 days ago
  • 1 min read

ታህሳስ 14/2018


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በተለያዩ ሀገሮች ተመድበው ሲሰሩ የቆዩ 29 የሀገሪቱን አምባሳደሮች ወደ አገር ቤት አስጠሯቸው፡፡


ወደ አገር ቤት የተጠሩት አምባሳደሮቹ በአፍሪካ ፣ በእስያ ፣ በምስራቅ አውሮፓ እና በላቲን አሜሪካ አገሮች ተመድበው ሲሰሩ የቆዩ መሆኑን AOL ፅፏል፡፡

ree

ትራምፕ በ47ኛ ፕሬዘዳንትነት ወደ ዋይት ሐውስ እንደተመለሱ በቀድሞው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደን የአስተዳደር ዘመን ተሾመው የነበሩ በርካታ አምባሳደሮችን እንዳባረሩ መረጃው አስታውሷል፡፡


ፕሬዘዳንቱ 29 አምባሳደሮችን ላባረሩበት እርምጃ የዋይት ሐውስ ሹሞች ይሄ የተለመደ አሰራር ነው ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


ትራምፕ የአሜሪካ ትቅደም አጀንዳቸውን የሚያራምዱላቸውን መርጠው የመሾም መብታቸው የተጠበቀ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


ከየሀላፊነታቸው የሚነሱት አምባሳደሮች በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ባልደረባነታቸው ግን አይባረሩም ተብሏል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page