top of page

የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል ታስቦ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ስርዓቱን ማሻሻያ አንዱ ቢሆንም እስካሁን ግን መፀሀፍቱን አሳትሞ ለተማሪዎች ማዳረስ አልተቻለም ተባለ።

  • May 19
  • 1 min read

ግንቦት 11/2018


የትምህርት ዘርፉን ለማሻሻል ታስቦ ከተከናወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት ስርዓቱን ማሻሻያ አንዱ ቢሆንም እስካሁን ግን መፀሀፍቱን አሳትሞ ለተማሪዎች ማዳረስ አልተቻለም ተባለ።


አንደኛ ደረጃ መፀሀፍትን ክልሎች በራሳቸው በጀት እንደሚያሳትሙ የተነገረ ሲሆን ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚያስፈልገውን መፀሀፍ የሚያቀርበው ደግሞ ትምህርት ሚኒስቴር ነው ብለዋል።


ብዙዎቹ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መማሪያ መፀሀፍት አንድ ለአንድ በሚባል ደረጃ መዳረሱን የተናገሩት የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ የመፅሀፍ ስርጭት እጥረቱ የሚስተዋለው በአንደኛ ደረጃ ላይ ነው ብለዋል፡፡


በዚህም የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች በአማካይ አንድ መፀሀፍ ለሶስት እና ለአራት ሆነው እንዲጠቀሙ እያደረገ እንደሆነም ነግሮናል፡፡

ከ200ሚሊየን ብር በላይ ወጭ አውጥቶ አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት የያዘውን መፀሀፍ በማሳተም ለተማሪዎች እያሰራጨ መሆኑን ያነሳው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ በበኩሉ አሁን ላይ አንድን መፀሀፍ ሁለት ተማሪዎች እየተጠቀሙበት ነው ብሏል፡፡


ከዚህ በኋላም አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት የያዘውን መፀሀፍ ለተማሪዎች አንድ በአንድ ለማዳረስ 4 ሚሊየን የሚጠጋ መፀሀፍ ማሳተም ይጠበቅብናል ሲል አስረድቷል።በተለይ ደግሞ የሰላም እጦት በነበሩባቸው እና አሁንም ድረስ በቀጠሉባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች አዲሱን ሥርዓተ ትምህርት የያዘውን መፀሀፍ ለማግኘት መቸገራቸውን ተደጋግሞ ሲነሳ ሰምተናል።


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….


ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…







 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page