የስራ ስምሪት ወደተደረገባቸው ሀገራት ሰራተኞች እየሄዱ ነው፡፡
- Jun 17
- 1 min read
ሰኔ 10/2018
የስራ ስምሪት ወደተደረገባቸው ሀገራት ሰራተኞች እየሄዱ ነው፡፡
አሁንም ግን በደላሎችና በኤጀንሲዎች ተታለው ወደ ውጪ ለስራ በህገ-ወጥ መንገድ የሚሄዱ አሉ፡፡
የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ይህንን ለማስቆም ምን እየሰራ ነው?
ህገ-ወጥ ስደትን ለመከላከል የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከተለያዩ የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ማለትም ከፍትህ ሚኒስቴር ፣ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከፌዴራል ፖሊስ ከኢሚግሬሽ እና ዜግነት አገልግሎት ጋር በጋር እየሰራ እንደሆነ ተናግሯል፡፡
በህገ ወጥ መንገድ ካናዳ እንልካችኋን እየተባሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች እየተጭበረበሩ እንደሆነ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተናግሯል፡፡
ኢትዮጵያ ወደ ካናዳ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለመላክ ስምምነት አድርጋለች ወይ? ካደረገች የስራ ስምሪት እየተደረገ ነው ወይ ? ስንል ጠይቀናል፡፡
በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የውጭ ሃገር የስራ ስምሪት ዴስክ ሃላፊ አቶ በዛብህ ከተማ ካናዳ ከሚገኝ አንድ ተቋም ጋር ስምምነት ተፈረመ እንጂ የስራ ስምሪት አልተጀመረም ሲሉ ነግረውናል፡፡
የስራ ስምሪት ሲጀመር መንግስት በሚዲያ ያሳውቃል እስከዛ ከመጭበርበር እና ገንዘባችሁን ከመበላት እራሳችሁን ጠብቁ ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…
ማርታ በቀለ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i





Comments