የሰለጠኑ ብቁ ወጣት ኢትዮጵያውያን በካናዳ የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ሚያስችል ስምምነት ተፈመ፡፡
- 6 hours ago
- 1 min read
ሚያዝያ 1/2018

የሰለጠኑ ብቁ ወጣት ኢትዮጵያውያን በካናዳ የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ ሚያስችል ስምምነት ተፈመ፡፡
ስምምነቱን የተፈራረሙት የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴርና ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል ድርጅት ነው፡፡
ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ ካናዳ ስራ ለማሰማራት ብቸኛው በመንግስት ፈቃድ የተሰጠው ተቋም መሆኑን የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
ፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል በማእድን ፣ በኢሮስፔስ ፣ በኮንስትራክሽንና በጤናው ዘርፍ የሚወጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችን መልምሎ በማሰልጠን ለስራ ዝግጁ እንደሚያደርግ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈርያት ካሚል ተናግረዋል፡፡
እነዚህ ወጣቶች የሚሰለጥኑት በካናዳ የስልጠና መስፈርት ነው የተባለ ሲሆን ምልመላውም በኢትዮጵያ ገበያ መረጃ ስርዓት አማካኝነት በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር በኩል እንደሚደረግ ተጠቅሷል፡፡
የሚሰለጥኑት ወጣቶች ለውጪ ገበያ ብቻ ሳይሆን ለሀገር ውስጥም ታሳቢ በማድረግ እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡
የፊውቸር ፊት ኢንተርናሽናል ድርጅት ኃላፊ አቶ አቢይ ራይሞንድ ቅድሚያ የአሰልጣኞች ስልጠና በመስጠት ስልጠናውን ማካሄድ እንጀምራለን ብለዋል፡፡
ብቁ ባለሙያዎችን በተገቢው መንገድ በመመልመል መስፈርቱ የሚያሟሉ ሰልጣኞችን በነፃ ስልጠናውን እንዲያገኙ ያስረዱ ሲሆን መስፈርት የማያሟሉ ሰዎችን በምንም መንገድ ስልጠናውን እንደማያገኙ ጠቅሰዋል፡፡
ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ይህ ስምምነት በካናዳ መንግስት እውቅና አለው ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር ኒኮላስ ሲማርድ በጤና ፣ ኮንስትራክሽን በማእድን ሀይል ፣ በአግሮ ፉድ ና በሌሎች ዘርፎች አሁን ስልጠናዎቹ ይሰጣሉ ሲሉም ተናግረዋል፡፡
የሁለቱ ሀገራ የኢኮኖሚ ትብብር ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣቱንም ጠቅሰዋል፡፡
አንዳንዶች ወደ ካናዳ ቪዛ እናሰጣለን እያሉ ማስታወቂያ ሲያስነግሩ እንሰማለን እንዲታወቀው የምንፈልገው ነገር ቪዛ ለማስጨረስ ከኤምባሲው ውጪ ምንም ተወካይም ሆነ ኤጀንት እንደሌለ ነው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ማስታወቂያውም በምንም ሁኔታ በቲክቶክና በሌሎች የማህበራዊ ሚዲያ እንደማይለቀቅና በስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ወይም በህጋዊ የሚዲያ ተቋማት በኩል ይፋ ይደረጋል ሲል የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡
በረከት አካሉ




Comments