top of page

ከክልሎች ጋር በመተባበር 1 ሺህ 452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት ማቀዱን የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ።

  • 1 hour ago
  • 1 min read

ሚያዝያ 20/2018

 


ከክልሎች ጋር በመተባበር 1 ሺህ 452  የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመገንባት ማቀዱን የትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ።

 

አዲስ የሚገነቡት ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ727 ወረዳዎች ውስጥ ነው ተብሏል፡፡

 

626 ትምህርት ሚኒስቴር የሚገነባ ሲሆን ቀሪው ደግሞ ክልሎች እራሳቸው እንደሚገነቡ ተነግሯል።

 

ለዚህ ስራ የሚያስፍልገው 40 ሚሊዮን ዶላር ከአጋር ድርጅቶች እርዳታ  ተገኝቷል ተብሏል።

 

እስካሁን 460 የሚሆኑ ኮንትራክተሮች የተመረጡ ሲሆን ቀሪው ደግሞ በሚቀጥሉት ጊዜያት ለመፈለግና በዚህ አመት ግንባታው አጠናቆ በ2019 ወደ ስራ ለመግባት መታቀዱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናግረዋል።

 

ይህ ስራ ሲጠናቀቅ 87 ሺ አዲስ ተማሪዎች ወደ ትምህርት እንዲቀላቀሉ ያደርጋል ተብሏል።

 

በሌላ በኩል የትምህርት ሚኒስቴር 36 ሚሊዮን የአንደኛ ደረጃ መፅሐፍትን ለማሳተም የመጨረሻ ደረጃ ላይ መድረሱን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስረድተዋል ። መፅሐፍቱ ለመጪው የትምህርት ዘመን ይደርሳል ያሉ ሲሆን በዚህ አመት 23 ሚሊዮን የአንደኛ ደረጃ መፅህፍት ማሳተሙና ማከፋፈሉን ተነግሯል።

 

በዚህ ስራም የመፅሐፍት ተማሪ ጥምርታው በአዲሱ የትምህርት አመት ወደ አንድ ለአንድ ይደርሳል ተብሏል።

 

በረከት አካሉ

Recent Posts

See All
በኢትዮጵያ በፋይናንስ ተቋሞች የተከፈተ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር ከ176 ሚሊየን በላይ ደርሷል።

ሚያዝያ 20/2018 በኢትዮጵያ በፋይናንስ ተቋሞች የተከፈተ የቁጠባ ሂሳብ ቁጥር ከ176 ሚሊየን በላይ ደርሷል። ከዚህ የባንክ ሂሳብ 97 በመቶው ግን ከ100 ሺህ ብር በታች ገንዘብ የተቀመጠበት መሆኑ ተነግሯል። በኢትዮጵያ የፋይናንስ ተቋሞች በኪሳራ ምክንያት ቢዘጉ ገንዘቡን የቆጠበው ሰው ያስቀመጠውን እ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page