top of page

ኢዮብ ተስፋ ለሕጻናትና ለወጣቶች በጎ አድራጎት ድርጅት፤ ለ3 የህክምና ተቋሞች የህክምና ቁሳቁሶችን አስረከበ።

  • May 6
  • 1 min read

ሚያዝያ 28/2018


ኢዮብ ተስፋ ለሕጻናትና ለወጣቶች በጎ አድራጎት ድርጅት፤ ለ3 የህክምና ተቋሞች 180 ሺህ ዶላር ወይም ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የህክምና ቁሳቁሶችን አስረከበ።


ድርጅቱ ለልብ ህክምና አገልግሎት የሚውሉትን የህክምና ቁሳቁሶቹ ያስረከበው ለጥቁር አንበሣ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፣ ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ እና ለኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ነው።


ኢዮብ ተስፋ ለሕጻናትና ለወጣቶች በጎ አድራጎት ድርጅት ከደጋፊዎቹ ባገኘነው ደጋፍና ትብብር የገዛናቸውንና አብረውት ከሚሰሩ የልብ ሐኪሞች ትብብር ከሜድትሮኒክ ኩባንያ ያገኘናቸውን በጠቅላይ 180,000 ዶላር ወይም ከ27 ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የሕከምና ቁሳቁሶችና መሳሪያዎችን ለሶስቱ ተቋሞች አስረክቧል።


ኢዮብ ተስፋ ለሕጻናትና ለወጣቶች በጎ አድራጎት ድርጅት በድንገተኛ የልብ ሕመም በ17 ዓመቱ እድሜው ሕይወቱ ባለፈው በኢዮብ አበባው ስም በወላጆችና በወዳጅ ዘመድ ትብብር የተቋቋመ በጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን ሰምተናል።


የበጎ አድራጎት ድርጅቱ ከ4 በፊት የተቋቋመው በሀገረ አሜሪካ ሲሆን በኢትዮጵያም የተመዘገበ ድርጅት እንደሆነ ተነግሯል።


የበጎ አድራጎት በተለይ በኢትዮጵያ በልብ ሕመም ለሚሰቃዩ ልጆችና ወጣቶች ቅድሚያ በመስጠት ነፍስ አድን የሆኑ የሕከምና ቁሳቁሶችንና መሳሪያዎችን በማቅረብ ላይ በርትቶ እየሰራ እንደሆነ የድርጀቱ መስራችና የእዮብ ወላጅ አባት አቶ አበባው አንበሣው አስረድተዋል።


ድርጅቱ ለጥቁር አንበሣ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ፣ ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ እና ለኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ከዚህ በፊትም የተለያዩ የህክምና ቁሳቁሶችን መስጠቱን ሲነገር ሰምተናል።


በድርጅቱ ቀጥተኛ ድጋፍ ብቻ በኢትዮጵያ ልብ ህሙማን ህጻናት መርጃ ማዕከል ብቻ 100 ህፃናት መታከማቸውን ሰምተናል።


በአጠቃላይም ኢዮብ ተስፋ ለሕጻናትና ለወጣቶች በጎ አድራጎት ድርጅት ለሶስቱ ህክምና ተቋሞች ባደረገው ድጋፍ የበርካታ ህፃናት ልብ መታከሙን የየሆስፒታሎቹ ሀላፊዎች ተናግረዋል፣ ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።


ድርጀቱ ወደፊትም ተመሳሳይ ድጋፎች እንደሚያደርግ ተናግሮ ለዚህም በየትኛውም የአለም ክፍል የሚገኙ ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች እጃቸውን እንዲዘረጉለት ጠይቋል።


ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


YouTube : https://shorturl.at/18TS1

WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx

X :- https://x.com/shegerfm?s=2

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page