top of page

ኢትዮጵያ እና ቻይና ባለፈው ዓመት 8.5 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡

  • Apr 28
  • 1 min read

ሚያዝያ 20/2018


ኢትዮጵያ እና ቻይና ባለፈው ዓመት 8.5 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡


ከዚህ ውስጥ 8 ቢሊዮን ዶላሩ ቻይና ወደ ኢትዮጵያ ሸቀጦቿን ልካ ያገኘቺው ገቢ ሲሆን ቀሪው 5 መቶ ሚሊዮን ዶላሩ የኢትዮጵያ ምርቶች በቻይና ገበያ ያወጡት ዋጋ ነው፡፡


በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ ሚዛን ልዩነቱ እጅግ ሰፊ ነው፡፡


የሁለቱ ሀገራት የንግድ ትስስር የበለጠ እንዲጠብቅ ካደረጉ ማህበራት መካከል የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክርቤት ቀዳሚው እንደሆነ ይነገራል፡፡


የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ፀሀፊ አቶ ካሳሁን ማሞ የሁለቱ ሀገራት የንግድ ትስስር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ይናገራሉ፡፡


የአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ቻይና ከሚገኙ የተለያዩ የንግድ ማህበራት ጋር የጋራ ስምምነት እየተዋዋለ መሆኑን የነገሩን ሲሆን ከቻይና በዋናነት ወደ ኢትዮጵ እየገቡ ያሉት ግዙፍ የፋብሪካ ማሽነሪዎችና የኤሌክትሮኒክስ ውጤቶች ፣ ለግንባታው ዘርፍ የሚያስፈልጉ ግብአቶች ተጠቃሽ መሆናቸውን ነግረውናል፡፡


ኢትዮጵያ በዓመት ለምታስገባው የገቢ ምርት  ወደ 24 ቢሊዮን ዶላር  የምታወጣ ሲሆን 8 ቢሊዮን የሚሆነው ከቻይና የሚመጣ የገቢ ምርት ነው፡፡


ታዲያ ኢትዮጵያውያን ነጋዴዎች የህን የንግድ ሚዛን ለማጥበብ ምን እየሰሩ ነው ? የንግድ ምክር ቤቱስ የሚያደርጋቸው ጥረቶች አለ ይሆን ስንል ምክትል ዋና ፀሀፊውን አቶ ካሳሁን ማሞን ጠይቀናቸዋል፡፡


በምላሻቸውም የሚላኩ ምርቶች እሴት እንዲጨመርባቸው ፣ ቻይናውያን ባለሀብቶችም ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥረት  እንደሚያደርጉ ጠቅሰዋል።


አሁን ላይ ከ5,000 በላይ የቻይና ባለሃብቶች ኢትዮጵያ ውስጥ በኢንቨስትመንት ስራ ላይ መሰማራታቸውን የነገሩን አቶ ካሳሁን ይህም ቻይናውያኑ እዚሁ ሀገር ቤት ምርቶቻቸውን እንዲያመርቱ ለማድረግና ያለው የንግድ ሚዛን ጉድለቱንም ለማጥበብ ይረዳል ብልዋል፡፡

ይህን ለማድረግም የኢትዮጵ ባለሃብቶችና የቻይና ባለሃብቶች አብረው የሚሰሩበት መንገዶችን እንደሚያመቻቹም አስረድተዋል፡፡


በረከት አካሉ

Recent Posts

See All
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page