top of page

ነሀሴ 6 2017 - ''በአቅሜ ልክ ግን እየሰራሁ አይደልም'' አምስተል ኢንቨስትመንት

  • sheger1021fm
  • Aug 12
  • 1 min read

አትክትልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ለረጅም ጊዜ ሳይበላሹ እንዲቆዩ በማድረግ ለገበያ እያቀረብኩ ቢሆንም በአቅሜ ልክ ግን እየሰራሁ አይደልም ሲል በዙርፉ የተሰማራው አምስተል ኢንቨስትመንት ተናገረ፡፡


ይህንን ስራ ለዓመታት እየሰራሁ ቢሆንም ዛሬም ድረስ በህብረተሰቡ ዘንድ እውቅና የለውም ብሏል፡፡


እንደ ካሮት፣ ድንች፣ ፎሶሊያ እና ሌሎች ፍራፍሬ እና አትክልቶች ተፀድተው እና ተከታትፈው በራሳቸው የሙቀት መጠን ፍሪጅ ውስጥ በማስቀመጥ ለምግብነት እንዲውሉ ማድረግ ላይ እንደሚሰራ ተናግሯል፡፡


እነዚህ ያለቀላቸው አትክልቶች የአመት እድሜ እንዲኖራቸው ተደርገው የተሰናዱ ናቸው ያሉት አምስተል ኢንቨስትመንት ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ እመቤት ታደሰ ምርቶቻችንን ለሆቴሎች እያቀረብን ነው ብለዋል፡፡


ፍራፍሬ እና አትክልቶች በዚህ ዓይነት መንገድ ተቀነባብረው ለአመት ሲቆዩ ተጠቃሚው ላይ ሊፈጥር የሚችለው የጤና ጉዳት ይኖር ይሆን? ስንል የጠየቅናቸው በአለም አቀፉ የምግብ ምርምር ፖሊሲ ኢንስቲቱት ተመራማሪ ሳይንቲስት የሆኑትን ዶክተር ታደሰ ዘርፉ እነዚህ ምርቶች ታሽገው ሲቀመጡ የራሳቸው በጎ ጎንም ቢኖራቸው ቢቻል ከቀናት ባዘል ካልሆነ ደግሞ ለተወሰኑ ከሳምንታት ብቻ ቢቀመጡ ጥሩ እንደሚሆን ምክረ ሀሳባቸውን ሰጥተውናል፡፡


ነገር ግን አትክልት እና ፍራፍሬዎቹ በእንዲህ ዓይነት መልኩ ታሽገው በቆዩ ጊዜ ተፈጥሮአዊ ይዘታቸውን እንዲቀይሩ ያደርጋቸዋል ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…….

ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page