ነሀሴ 27 2017 - የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ "የትውልድ አሻራ" የተሰኘ የመልካም ምኞት ማስተላለፊያና የገንዘብ መላኪያ አጭር ቁጥር ይፋ ተደርጓል
- sheger1021fm
- Sep 2
- 1 min read
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ዛሬ ያስተዋወቀው አጭር ቁጥር 8120 ሲሆን መርሃ ግብሩም «የትውልድ አሻራ - ዲጂታል የብስራት መልዕክትና ገቢ ማስገኛ ፕሮጀክት" የሚል ስያሜ የተሰጠው መሆኑንም ሰምተናል።
የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር አረጋዊ በርሄ የአጭር የፅሁፍ መልዕክት መላኪያ መስመሩ አላማ ሲያስረዱ ህዝቡ በሚልከው መልዕክት አሻራውን ለታሪክ እንዲያስቀመጥ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
መልዕክቶቹ ሲላኩ በአንድ መልዕክት ለግድቡ 20 ብር ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻልና በመላኪያ ቁጥሩ የሚመጡ አማራጮችን በመምረጥ ከ5 ብር ጀምሮ እስከ መቶ ብር ድረስ ድጋፍ ማድረግ እንደሚቻልም ተናግረዋል፡፡
መርሀ ግብሩ ከዛሬ ነሀሴ 27 ቀን 2017 ጀምሮ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 የሚቆይ መሆኑንም እወቁት ብለዋል።
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s












Comments