top of page

ነሀሴ 22 2017 - አቢሲኒያ ባንክ ከፋስትፔይ ጋር በጋራ ሊሰራ መሆኑን ተናገረ፡፡

  • sheger1021fm
  • 2 days ago
  • 1 min read

አቢሲኒያ ባንክ እየሰጠ ያለውን አለም አቀፍ ዲጅታል የሀዋላ አገልግሎት ይበልጥ ለማቀላጠፍ ከፋስትፔይ ጋር በጋራ ሊሰራ መሆኑን ተናገረ፡፡


ባንኩ ለዚሁ ስራ መቀላጠፍ መቀመጫውን በአሜሪካ ካደረገው እና በትዮጵያ ቅርንጫፍ ቢሮ ከከፈተው ፋስትፔይ (FastPay) ከተሰኘ የዲጅታል ኩባንያ ጋር ዛሬ ውል አስራለሁ ብሏል፡፡


አቢሲያ ባንክ ከፋስትፔይ (FastPay) ዲጅታል ጋር በጋራ የሚሰጠው አለም አቀፍ ዲጅታል የሀዋላ አገልግሎትን ለማቀላጠፍም የሳይበርሶርስ (Cyber Source) የክፍያ አማራጭ ቴክኖሎጅን መስርቷል ተብሏል፡፡


በፋስት ፔይ መተግበሪያ አማካይነት በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቪዛ ወይም የማስተር ካርዳቸውን ተጠቅመው ወደ ሀገር ቤት በሀዋላ ገንዘብ ሲልኩ ባንኩ እዚህ ላሉ ወዳጅ ዘመዶቻቸው ክፍያውን የማቀላተፍ ድርሻዬን እወጣለሁ ብሏል፡፡


አቢሲኒያ ባንክ ባሰናዳው አለም አቀፍ የዲጅታል የሀዋላ አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቅድሚያ በመተግበሪያው መመዝገብ ይኖርባቸዋል ተብሏል፡፡


በዚህም የደንበኞች የክፍያ ካርድ ከአለም አቀፍ የቪዛ ወይም የማስተር ካርድ አገልግሎት ጋር የሚተሳሰር ሲሆን በዚሁ የተሳሰረ ስርዓት ተተቅመው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቀላሉ ገንዘብ ወደ ሀገር ቤት መላክ ይችላሉ ብሏል ባንኩ፡፡


አቢሲኒያ ባንክ እና ፋስት ፔይ (FastPay) ይፋ ያደረጉት የተጠቀሰው አለም አቀፍ የዲጅታል የሃዋላ አገልግሎት የውጭ ምንዛሬ የማግኘት አቅምን ከፍ ያደርጋል ተብሎለታል፡፡


እንዲሁም ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከሌሎች የሀዋላ መላኪያ ዘዴዎቸ በተሸለ እና ከአልግሎት ክፍያም ነፃ የዲጅታል የገንዘብ የመላኪያ አማራጭ እንዲኖራችም ያስችላል ተብሏል፡፡


በተጨማሪም በኢመደበኛ መንገድ የሚደረገውን የሀዋላ ዝውውር ለመቀነስ መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ ያግዛል ብሎ እንደሚያምንም አቢሲኒያ ባንክ በላከልን መግለጫ ተናግሯል፡፡


ባንኩ ባለፉት 29 ዓመታት የተለያዩ ዘመናዊ የባንክ ቴክኖሎጅዎችን ስራ ላይ በማዋል ደንበኞቹን እያገለገለ መሆኑን አስታውሷል፡፡


ፋስት ፔይ አለማቀፍ ዲጅታል የሀዋላ አገልግሎት ቴክኖሎጅን አበልፅጎ ከአቢሲንያ ባንክ ጋር ለመስራት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ውል ያስራል የተባለው FastPay digital LLC የተሰኘው ተቋም ዋና መቀመጫው በአሜሪካ መሆኑን ሰምተናል፡፡


ትዕግስት ዘሪሁን


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




1 Comment


Anika sharma
Anika sharma
11 hours ago

With the Call Girls In Mumbai, I had the most incredible experience. Because of our genuine connection and the ease with which we conversed, the occasion felt genuine and valuable.

Like
Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page