top of page

ነሀሴ 21 2017 - የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከ10,000 በላይ የቀድሞ የጉህዴን እና የቤህነን ታጣቂዎች ሰልጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረጉን ተናገረ።

  • sheger1021fm
  • Aug 27
  • 1 min read

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከ10,000 በላይ የቀድሞ የጉህዴን እና የቤህነን ታጣቂዎች ሰልጥነው ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረጉን ተናገረ።


የስራ ዕድሉ የተፈጠረላቸው ሰዎች ውጤታማነት ግን ይለያያል ብሏል።


የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ጉህዴን) እና የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነጻነት ንቅናቄ(ቤህነን) ከሶስት ዓመት በፊት ከክልሉ መንግስት ጋር የሠላም ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።


የስምምነቱ አንዱ ይዘት የሁለቱ ቡድኖች የቀድሞ ታጣቂዎች ስልጠና ወስደው በተለያዩ ስራዎች እንዲሰማሩ የክልሉ መንግስት ያደርጋል የሚል ነው።


በዚሁ መሰረት እስከ አሁን ከ10,000 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎች ሰልጥነው በተለያዩ ስራዎች እንደተሰማሩ የክልሉ የስራ እና ክህሎት ቢሮ ሃላፊ አቶ አብዱሰላም ሸንገል ተናግረዋል።

ree

ግብርና፤ ኢንዱስትሪ እና አገልግሎት ደግሞ የተሰማሩባቸው የስራ መስኮች እንደሆኑ ጠቅሰዋል።


የቤንሻኒጉል ጉሙዝ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎች እስከ ሰኔ 30 /2017 ድረስ አቋቁሞ ለመጨረስ አስቀምጦት የነበረውን የጊዜ ገደብ ባለፈው መጋቢት ወር በአንድ ዓመት ማራዘሙ ይታወሳል።


ስራውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ማከናወን እንደማይቻል በመረጋገጡ የማራዘም ውሳኔው እንደተላለፈ ነው በወቅቱ የተነገረው።


የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ተመላሾችን ለማቋቋም እና ወደ ስራ ለማስገባት ልዩ መመሪያ ያፀደቀው በ2015 ዓ/ም የካቲት ወር ላይ ነበር።


ስራውን እንዲመራም ለክልሉ ስራ እና ክህሎት ቢሮ ሃላፊነት ሰጥቷል፡፡


ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page