top of page

ነሀሴ 21 2017 - የስታርት አፕ አዋጅ በጤናው ዘርፍ ለሚከወኑ የተሻሻሉና ዘመናዊ አሰራሮችን ለመተግበር ያግዛል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Aug 27
  • 1 min read

በቅርቡ የፀደቀውና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን ያበረታታል የተባለው የስታርት አፕ አዋጅ በጤናው ዘርፍ ለሚከወኑ የተሻሻሉና ዘመናዊ አሰራሮችን ለመተግበር ያግዛል ተባለ፡፡


በጤና ዘርፉ ከሚሰጡ አገልግሎቶችም ስምንቱ በተለይ በኢኖቬሽን የተደገፈ አሰራር እንዲከተሉ እየተደረገ ነው ተብሏል፡፡


በተለያዩ የጤና አገልግሎት መስጫዎች ላይ ዘመናዊ አሰራሮችን ለመከተል እና በተለይም አገልግሎቶችን ከማሻሻል አኳያ የጤና ኢኖቬሽን ላይ ትኩረት ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

ree

አቶ ደነቀ አየለ በጤና ሚኒስቴር የጤና ሥርዓት ኢኖቬሽንና ጥራት መሪ ስራ አስፈጻሚ ክፍል አስተባባሪ ናቸው፡፡


በጤናው ዘርፍ የተሻሻለው ፖሊሲ በተለይ ዘመናዊ አሰራሮችን በአገልግሎቱ ላይ መተግባር አንድ የተቀመጠ ግብ በመሆኑ በስፋት እንዲሰራበት ለማድረግ የጀመርናቸው ስራዎች አሉ ብለዋል፡፡


ኢኖቬሽንን በተለያዩ ዘርፎች ለመተግበር ሁለተኛ ዙር ፖሊሲ ወደ ስራ መግባቱን የሚጠቅሱት አቶ ደነቀ በስራው ላይ ያሉትን ሂደቶች በተመለከተ በጤናው ላይ በየጊዜው ግምገማ እንደሚደረግበት ይናገራሉ፡፡


ከጤና አገልግሎቶች ውስጥም ተላላፊ ያልሆኑ ህመሞች፣ የእናቶችና ህፃናት ጤና እና ሌሎች 6 አገልግሎቶች ተለይተው የህክምና እና መከላከል ስራዎችን በዘመናዊ አሰራር ለመደገፍ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመሆን እየተተገበሩ ያሉ አሰራሮች አሉ ብለዋል አቶ ደነቀ፡፡


በኢትዮጵያ በቅርብ ዓመታት በጤና ተቋማት ላይ ፈጠራን እንዲሁም የተገልጋዮችን እንግልት እንዲቀንሱ በሚል የተተገበሩ የኢኖቬሽን ስራዎች ከዚህ ቀደም የሚታዩ ችግሮችን እንዲሻሻሉ ማድረጉ ተነግሯል፡፡


ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚከወኑ የጤናው ዘርፍ አገልግሎቶች ማሻሻያ በተለይ የአገልግሎት ጥራትና ደህንነት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለማስወገድም የሚያግዝ ነው ሲል የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….


ምህረት ስዩም


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page