ነሀሴ 20 2017 - የዶሮ መኖ ላይ የተጣለው የ15 በመቶ የቫት ክፍያ
- sheger1021fm
- Aug 26
- 1 min read
ለዶሮና እንቁላል ዋጋ መናር ምክንያት የሆኑ የዶሮ መኖ መወደድ እና የቫት ክፍያ መጨመሩ አምራቾችንም ከገበያ እያስወጣቸው መሆኑ ይነገራል፡፡
ችግሩ መላ እንዲሰጠው የዶሮ መኖ ላይ የተጣለው የ15 በመቶ የቫት ክፍያም ቀሪ እንዲደረግ ጠይቄ ምላሽ ባለማግኘቴ ችግሩ ቀጥሏል ይላል የኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎች እና አቀነባባሪዎች ማህበር፡፡
የማህበሩ ስራ አስኪያጅ አቶ ዝናው ፀሀይ ነህ ከዚህ ቀደም ካነሳናቸው ችግሮች መካከል የተፈቱልን ቢኖሩም የቫት ክፍያና የመኖ ዋጋ መናር ግን እስካሁን አልተፈቱልንም ብለዋል።
የቫት ክፍያን በተመለከተ እስከ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድረስ ጉዳያችን ሄዷል ሆኖም እስካሁን ምንም ዓይነት እልባት አላገኘንም ሲሉም ነግረውናል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/634ecb/
ፍቅሩ አምባቸው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s











Comments