ነሀሴ 19 2017 - የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች እና የኮሪደር ስራን የሚቆጣጠርና የሚመራ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተቋቋመለት
- sheger1021fm
- Aug 26
- 1 min read
የአዲስ አበባን የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች እና የኮሪደር ስራን የሚቆጣጠርና የሚመራ ባለስልጣን መስሪያ ቤት ተቋቋመለት፡፡
እስካሁን የተሰሩና ከዚህ በውሃላም የሚሰሩ የወንዝ ዳርና የኮሪደር ልማት ስራዎችን የሚመራና የሚቆጣጠር የኮሪደርና የወንዝ ዳር ፕሮጀክቶች መቆጣጠርና ማስተዳደር ባለስልጣን ተቋም በከተማ አስተዳደሩ መመስረቱን ሰምተናል።
ለአዲስ አበባ የመጀመሪያው የሆነውና በግንባታ ላይ ያለው ከእንጦጦ እስከ ፒኮክ መናፈሻ የሚደርሰው የ21.5 ኪ.ሜ የወንዝ ዳር ፕሮጀክት ስራ 90 በመቶ መድረሱንም የአዲስ አበባ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን ምክትል ስራ አስፈፃሚና የአዲስ አበባ የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ኮሪደር ልማት ምክትል አስተባባሪ አቶ ዋለልኝ ደሳለኝ ነግረውናል።
እስከ መጪው ጥቅምት ወር መጨረሻም አጠቃላይ ስራው ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡
ከዚህ በኋላም ስራውን የሚቆጣጠርና የሚከታተል ተቋም መቋቋሙን ተከትሎም የወንዝ ዳር ፕሮጀክቱ ያለምንም መቆራረጥ በቋሚነት የሚሰራ እንደሚሆንም ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ....
ቴዎድሮስ ወርቁ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
Comments