top of page

ነሀሴ 19 2017 - የቤት ሰሪዎች የግብዓት የኦንላይን ገበያ ተከፈተ

  • sheger1021fm
  • Aug 26
  • 1 min read

የግንባታ እቃዎችን፣ የፈርኒቸር ምርቶችና የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎችን በአንድ የያዘ የኦላይን ገበያ መከፈቱን ሰምተናል፡፡


በዚህ ገበያ የቀረቡት እቃዎች በመደበኛው ገበያ እንደልብ የማይገኙ በመሆናቸው ብዙዎች ከውጭ የሚያስመጧቸው በመሆኑ ወደዚህ የኦላይን ገበያ መግባታቸው ከውጭ በማስመጣት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪን የሚያስቀር ነው ተብሏል፡፡


እነዚህን ሁሉን በአንድ የያዘ፤ የውጭ ምንዛሪንም ያስቀራል የተባለለት ገበያ በኦላይን ተከፍቷል መባሉን ሰምተናል።


ይህ የኦላይን ገበያ በቅዱስ ማርቆስ የእንጨት ስራዎችና ኢንቲሪየር ዲዛይን ድርጅት ተከፍቷል።


''Km living by kidus markos'' በተሰኘው የኦላይን ገበያ ከ14 በላይ ሃገር በቀል ድርጅቶችና አስመጪዎች የፈርኒቸር፤ የግንባታ እቃዎችንና ሌላውንም የቤት ውስጥ መገልገያ ምርቶቻቸውን አቅርበዋል ያሉን የገበያው መስራች የሆኑት አቶ ቅዱስ ማርቆስ ናቸው።


የሚፈልጉትን ዓይነት እቃ በኦላይን በቀጥታ ማዘዝ የሚያስችለው መተግበሪያው የምርጫቸው የሆኑ የቤት እቃዎችን ለማግኘት ላይ ታች ማለትን እንደሚያስቀር እንዲሁም ከውጪ ለማምጣት የሚወጣውን የውጭ ምንዛሪ ለማዳን ታስቦ የተሰናዳ በሆኑን አቶ ቅዱስ አስረድተዋል።


ምርታቸውን ለመሸጥ ወደ መተግበሪያው ለሚገቡ ድርጅቶች ዋናው መስፈርት የምርታቸው ወጥ የሆነ ጥራትና ቢዝነሱ ቀጣይነት ያለው መሆኑ እንደሆነ የነገሩን መስራቹ፤ ትልቁ ፈተና የነበረው ተቋማቱ በመተግበሪያው አምነው ምርታቸውን ወደ መተግበሪያው እንዲያስገቡ ማሳመን እንደነበርም አንስተዋል።


''Km living by kidus markos'' የተሰኘውን መተግበሪያ በማሳደግም እንደ አማዞን ያለ ሁሉም ነገር የሚገኝበት ገበያ የማድረግ ውጥን እንዳላቸውም ነግረውናል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page