top of page

ነሀሴ 15 2017 - የግብአት እጥረት የኢትዮጵያ የግንባታ ዘርፍ ዋነኛው ፈተና ሆኖ በተደጋጋሚ ይነሳል

  • sheger1021fm
  • Aug 21
  • 1 min read

ሲሚንቶ፣ ብረት፣ እምነበረድ ወዘተ ማግኘት ከብዷቸው ለሠራተኞቻቸው እንኳን ደመወዝ መከፈል የተቸገሩ ተቋራጮች ብዙ እንደሆኑ ሠምተናል።


ሲሚንቶን ብቻ ብናነሳ እስከ ቅርብ ጊዜ ዓመታዊ ፍላጎቱ 20 ሚሊየን ቶን ሆኖ ሳለ አቅርቦቱ ግን ከ 7 ሚሊየን ቶን ያልበለጠ ነበር።


በርግጥ በቀን 150 ኩንታል የማምረት አቅም ያለው የለሚ ሲሚንቶ ፋብሪካ ባለፈው መስከረም ወር ተመርቆ ጥር ላይ ፤ ምርት ለገበያ ማቅረብ ከጀመረ በኋላ ይህ የአቅርቦትና ፍላጎት ክፍተት መጥበቡ ተነግሯል።


ፋብሪካው ስድስት ወራት ጊዜ ብቻ ከ12 ሚሊየን ኩንታል በላይ ሲሚንቶ ለገበያ አቅርቧል ተብሏል።


ሲሚንቶ ላይ የነበረው ችግር የምርትና አቅርቦት ጉዳይ ብቻ እንዳልሆነ የሚናገረው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር በበኩሉ ገበያውም ክፍተት እንደነበረበት ጠቅሷል።

ree

በሀገር ውስጥ እጥረት እያለ በህገ ወጥ መንገድ ወደ ውጪ ሁሉ ይላክ እንደነበር የሚኒስቴሩ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ኢትዮጵያ በዴቻ ተናግረዋል።


አሁን ላይ #የሲሚንቶ_ምርት አቅርቦት በገበያው ጥሩ እንደሆነ የሚናገሩት አቶ ኢትዮጵያ ወደፊት ግን ፍላጎቱ ማደጉ አይቀርም ብለዋል።


ይህን የሚያደግ ፍላጎት ለመሸፈን ደግሞ ተጨማሪ ፋብሪካዎች መገንባት እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት።


ሌላው የኮንስትራክሽን ዘርፍ ቁልፍ ግብአት ብረት ነው። ኢትዮጵያ ይህንን ግብአት በአብዛኛው ከውጪ እንደምታስገባ ይታወቃል።


በርግጥ በተጠናቀቀው በጀት በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የብረት ውጤቶች በ18 በመቶ ማደጋቸውን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ባለፈው ሰኔ ወር ለፓርላማ አባላት ማብራሪያ ሲሰጡ ተናግረዋል።


የብረት ፍላጎትን ሙሉ ለሙሉ ማሟላት የሚያስችሉ ስራዎችም ተጀምረዋል ብለዋል።


ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከ1 ቢሊዮን ቶን በላይ የብረት ማዕድን ክምችት በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ይገኛል፡፡


ይህን የብረት ማዕድን በማውጣት ጥቅም ላይ ለማዋል ምን እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ኢትዮጵያ ነግረውናል።


ሌሎች የዘርፉ ግብአቶችም ችግር ሆነው እንዳይቀጥሉ በምርምር ጭምር የተደገፈ ስራ እየሰራን ነው ሲሉ ስራ አስፈጻሚው ነግረውናል።


የኮንስትራክሽን ግብአቶች በሀገር ውስጥ እንዲሟሉ ማድረግ ከዋጋ ጋር ተያይዞ የሚነሳውንም ችግር እንደሚያስቀረው የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ተናግሯል።


ንጋቱ ረጋሳ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page