ነሀሴ 15 2017 - በፖለቲካ አቋማቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ወጥተው በሰሜን አሜሪካ እና በካናዳ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊን ጋር ምክክር ለማድረግ የምክክር ከሚሽን ኮሚሽነሮች በዚህ ሳምንት ወደ ስፍራው ያቀናሉ ተባለ
- sheger1021fm
- Aug 21
- 1 min read
በፖለቲካ አቋማቸው እና በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ወጥተው በሰሜን አሜሪካ እና በካናዳ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊን ጋር ምክክር ለማድረግ የምክክር ከሚሽን ኮሚሽነሮች በዚህ ሳምንት ወደ ስፍራው ያቀናሉ ተባለ፡፡
ይህን ያለው የሀገራዊ ምክከር ኮሚሽን ነው፡፡
በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ምክክር ለማድረግ እና አጃንዳዎቻቸውን ለመረከብ ዝግጅት ማጠናቀቁን የተናገረው ኮሚሽኑ ከምክክሩ በፊት በኮሚሽኑ ላይ የሃሳብ ልዩነት ያላቸውን አካላት አስቀድሞ ለማነጋገር እና በምክሩ እንዲሳተፉ ለመጠየቅ የሚስችል ወይይት እንደሚካሄድ ተነግሯል፡፡
የኮሚሽኑ ቃል አቀባይ አቶ ጥበቡ ታደሰ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሰፋ ያሉ የሀሳብ ልዩነቶች እና በአገራዊ ጉዳዮችም ላይም አለመግባባቶች ከሚታይባቸው ወገኞች መካከል ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል፡፡
እነዚህን የሀሳብ ልዩነቶች እና አለመግባባቶች ለይቶ በምክክር መፍታት እንደሚያስፈልግ የተናገሩት አቶ ጥበቡ ለዚህም እንዲረዳ ደግሞ ዝግጅት እየተደረገ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡
በኮሚሽኑ በኩል ተነጋግሮ ችግሮችን መፍታት አይቻልም የሚልንም ወገን ሆነ ተነጋግሮ ችግሮችን መፍታት ይቻላል የሚሉትን አካላት ለማሳተፍ እየተሰራ እንዳለ ተናግሯል፡፡
ያሬድ እንዳሻው








