top of page

ነሀሴ 13 2017 - ዜሌንስኪ በሰላሙ ጉዳይ ከሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ዝግጁ ስለመሆናቸው ፍንጭ ሰጡ፡፡

  • sheger1021fm
  • 3 days ago
  • 1 min read

የዩክሬይኑ ፕሬዘዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ በሰላሙ ጉዳይ ከሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ፊት ለፊት ለመነጋገር ዝግጁ ስለመሆናቸው ፍንጭ ሰጡ፡፡


ዜሌንስኪ ከፑቲን ጋር ለመነጋገር ፈቃደኝነታቸውን ያሳዩት በዋይት ሐውስ የአውሮፓ መሪዎች በተገኙበት ከአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ከተመካከሩ በኋላ ነው፡፡


ከዋይት ሐውሱ ንግግር አስቀድሞ ትራምፕ ሁሉም እንዲሰማ አድርገው ለሩሲያው ፕሬዘዳንት ስልክ ደውለውላቸዋል ተብሏል፡፡

ree

ይሄን ተከትሎ እንደማስበው ፑቲንም ሰላሙን ይፈልጉታል ሲሉ ተናግረዋል ትራምፕ፡፡


ትራምፕ የሩሲያ እና የዩክሬይን መሪዎች ለሰላም ፊት ለፊት ተገናኝተው እንዲነጋገሩ ሒደቱ ተጀምሯል ብለዋል፡፡


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ከዋይት ሐውሱ ምክክር አስቀድሞ ዩክሬይን እንደ ክራይሚያ ያሉ ግዛቶችን መልሳ አትጠይቅም ፣ የኔቶ አባልም አትሆንም ብለው ነበር፡፡


በዋይት ሐውሱ ንግግር ወቅት ግን ይህ ጉዳይ እንዳልተነሳ ቢቢሲ ፅፏል፡፡


የአውሮፓ መሪዎቹ ከማንኛውም የሰላም ንግግር ፊት የተኩስ አቁም አለመደረጉ ቅር አሰኝቷቸዋል ተብሏል፡፡


የፈረንሳዩ ፕሬዘዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የሰላም ጥረቱ ከከሸፈ በሩሲያ ላይ ከእስካሁኑ የከበደ ማዕቀብ ይጣልባት ማለታቸው ተሰምቷል፡፡


የብሪታንያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኪየር ስታርመር ግን የዋይት ሐውሱን ንግግር ታላቅ እርምጃ ማለታቸውን አልጀዚራ ፅፏል፡፡


የኔነህ ከበደ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page