top of page

ነሀሴ 1 2017 - ጌትስ ፋውንዴሽን ከ2025 እስከ 2030 እ.ኤ.አ ባሉት ዓመታት የእናቶችና የወጣት ሴቶችን ጤና ለመጠበቅ ቢሊዮን ዶላሮችን መመደቡን ተናገረ

  • sheger1021fm
  • Aug 7
  • 1 min read

ጌትስ ፋውንዴሽን ( #Gates_Foundation ) ከ2025 እስከ 2030 እ.ኤ.አ ባሉት ዓመታት የእናቶችና የወጣት ሴቶችን ጤና ለመጠበቅ ቢሊዮን ዶላሮችን መመደቡን ተናገረ፡፡


ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ የሚመሩት ጌትስ ፋውንዴሽን እናቶችና ወጣት ሴቶች በተላላፊ በሽታዎች እንዳይሞቱ መጪው ትውልድ በገዳይ በሽታዎች እንዳይጠቃ እና ሚሊዮኖችም ከድህነት እንዲወጡ ያግዛል ያለውን 2.5 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን ፋውንዴሽኑ ከላልን መልዕክት ተመልክተናል፡፡


በታዳጊ ሀገራት የሚገኙ እናቶችና ህፃናትን ከተላላፊ እና ከገዳይ በሽታዎች ለመታደግ ከ2000 እስከ 2025 በነበሩት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች ከመቶ ሚሊዮኖች በላይ የሚሆኑ ሰዎቹን ማትረፍ ተችሏል ያለው ፋውንዴሽኑ የመጪውን ጊዜ ስራም አጠንክሮ ለመቀጠል 2.5 ቢሊዮን ዶላር መመደቡን ተናግሯል፡፡


የድርጅቱ የበላይ ቢሊየነሩ ቢል ጌትስ በመጪዎቹ 20 ዓመታት ያለኝን ከ200 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሕይወት እያለሁ ለአገልግሎት አውየው እና ደህይቼ እሞታለሁ ብለው በቅርቡ ከተናገሩ በኋላ አሁን ይፋ የሆነው የድጋፍ ገንዘብ የመጀመሪያው ነው ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…… https://www.mixcloud.com/ShegerFM/76y457/

የኔነህ ሲሳይ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page