top of page

ብዙ ሰው የኩላሊት ህመምተኛ እየሆነ ያለው ለምንድነው?

  • sheger1021fm
  • Sep 19
  • 1 min read

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቅርብም በርቀትም የኩላሊት ህመምተኛ የሆኑ ሰዎችን  እያየን እየሰማን ነው፡፡ ጎዳና ወጥተው እርዳታ ለመጠየቅ የተገደዱም አሉ፡፡


በኢትዮጵያ አሳሳቢ የህብረተሰብ የጤና ጉዳይ እየሆነ የመጣው ይኸ በሽታ ለመሆኑ መንስኤው ምንድነው?


➤ የደም ግፊት


በኢትዮጵያ ውስጥ በጣም እየተለመደ ከመጣ እና ሥር ከሰደዱ በሽታዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ከፍተኛ የደም ግፊት በኩላሊት ውስጥ በሚገኙ ቀጭን የደም ሥሮች ላይ የማያቋርጥ ጫና በመፍጠር ለኩላሊት በሽታ ተጋላጭ ያደርጋል።


➤ የስኳር በሽታ


የስኳር በሽታ በተለይም “type 2” የሚባለው ተገቢውን ህክምና ካላገኘ ቀስ በቀስ የአካል ክፍሎችን ኩላሊትን ይጎዳል።


➤ ዕድሜ


ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እደሜያቸው 60ና ከዚያ በላይ የሆናቸው ሰዎች አረጋውያን ለኩላሊት በሽታ የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው።

ree

ታዲያ ምን እናድርግ..


የቅድመ ምርመራ ፣ የጤና አገልግሎት አቅርቦት እና በመረጃዎች ውስንነት የተነሳ አብዛኛዎቹ የኩላሊት በሽታዎች የሚታወቁት በጣም ዘግይተው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ሲደርሱ ነው።


የኩላሊት በሽታ በባህሪው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ካልደረሰ በቀር የሚያሳየው ልዩ ምልክት አለመኖሩ ከባድ ስለሚያደርገው ቢያንስ በአመት አንዴ የሽንት ምርመራ ማድረግን ዶክተሮች አብዝተው ይመክራሉ።


የአኗኗር ዘይቤ ለውጦች ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አለማድረግ፣ ጎጂ የሆኑ የአመጋገብ ልማዶቸ ለኩላሊት በሽታ መጨመር እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ።


የኩላሊት ጤናን ለመጠበቅ በቂ ውሃ መጠጣት ፣ ጨው እና ስኳር መቀነስ ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ እና ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ሥርዓትን መከተል ያስፈልጋል። ጤናዎን ይጠብቁ።


©️መረጃዎቹን ከቢቢሲ እና ናሽናል ላይብረሪ ኦፍ ሜዲስን ላይ ተመልክተናል፡፡


መስከረም 8 2018


ትዕግሥት ፍሰሃ




Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page