top of page

ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በካርበን ግብይት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተሰናዳ።

  • 3 minutes ago
  • 2 min read

ሰኔ 16/2018


ባንኮች እና የፋይናንስ ተቋማት በካርበን ግብይት ውስጥ እንዲሳተፉ የሚፈቅድ ረቂቅ አዋጅ ተሰናዳ።


በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላንና ፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ትናንት ሰኔ 15 ቀን 2018 ዓ.ም የአስረጂ ወይይት ያካሄደበት የካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ ባንኮች በካርበን ግብይት አንዲሳተፉ ይፈቅዳል።


ረቂቅ አዋጁ የተበታተነውን የካርበን ግብይት በአንድ የሕግ ማዕቀፍ ለማስተዳደር እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል እየተከናወኑ ያሉ ጅምር ስራዎችን ለማጠናከር እንደሚረዳ ተነግሯል።


ኢትዮጵያ ለአየር ንብርት ለውጥ ተጋላጭ መሆኗን ያስታወሰው የካርበን ረቂቅ አዋጅ ለአማቂ ጋዝ ልቀት ቅነሳ ደጋፍ ማድረግ እና በአየር ንብርት ለውጥ ላይ አደገኛ ጣልቃ ገብነትን ማስቀረት "የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ነው" ብሏል።



በአስር ክፍል በ44 ገጽ የተሰናደው የካርበን ረቂቅ አዋጅ የኢትዮጵያ በጉዳዩ ላይ በአለም አቀፍ ደረጃ የተፈራረመችውን ስምምነት ለመተግበርም እንደሚረዳ በአላማዎቹ ስር ተጠቅሷል።


ረቂቁ ስለ ፋይናንስ ድንጋጌዎች በሚዘረዝርበት ክፍል ዘጠኝ ላይ የባንኮችና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ተሳትፎ እና ሚና ሲያስረዳ ፤ ባንኮች እንደየፍላጎታቸው በገዥነት፣ በሻጭነት፣ በግብይት አከናዋኝነት ወይም አሰባሳቢነት ሊሳተፉ ይችላሉ ይላል።


የካርበን አሰባሳቢ የሚለው ሲተረጉመው ደግሞ ፤ ከተለያዩ የመሬት ባለይዞታዎች ፣ ኩባንያዎች አነስተኛ የሙቀት አማቂ ጋዞችን የመቀነስ፣ የማስወገድ ወይም የማስቀረት ፕሮጀክቶችን በአንድ ላይ በማሰባሰብ ወደ ልዩ ልዩ ፖርቶፎሊዮች በማካተት እንደገና የሚሸጥበትን መንገድ የሚመራ ነው ሲል ተርጉሞታል።


በተጨማሪም ባንኮች የካርቦን ሃብት ፖርቶፊሊዮችን ከአካባቢ እና ከማህበራዊ ስጋት አስተዳደር ማዕቀፎቻቸው ጋር እንዲገናኙ ይበረታታሉ ፣ ከካርበን ክሬዲት ጋር የሚያያዙ ቦንዶችን እና "አረንጓዴ ዋስትናዎችን "ጨምሮ ልዪ የፋይናንስ አግልግሎቶችን ማቀረብ እንደሚችሉ አስረድቷል።


ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ባንኮች ፣ የፋይናንስ ተቋማት በሀገሪቱ ለሚከናወኑ የሙቀት አማቂ ጋዞችን ልቀት ለመቀነስ ፣ ለማስቀረት አልያም ለማስወገድ ለተቀረጹ ፖሊሲዎች የብድር ፋይናንስ ፣ የኢኪዮቲ ኢንቨስትመንት እና የብድር ገጽታ፣ ማሻሻያዎችን ሊያቀርቡ እንደሚችሉም በረቂቁ ተደንግጓል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ለካርበን ክሬዲቶች ግብይት ፣ ዝውውር እና ክፍያ እንደ አሳላጫ ወይም ባለዳራዎች መሆን እንደሚችሉም ተጠቅሷል።


በካርበን ገበያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ወደፊት የሕዝብ ይፋዊ ውይይት መድረክ እንደሚካሄድ ተነግሯል።


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


 
 
 

Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ የመማር ማስተማር ሂደቱን እያወኩ ነው የተባሉ እንደ መጠጥ ቤት እና መሰል የንግድ ቤቶችን ከመማሪያ ቤት እንዲርቁ እየተሰራ ቢሆንም ውጤቱ ግን ውሃ ቅዳ ውሃ ምልስ ሆኗል ይላል የከተማዋ ትምህርት ቢሮ፡፡

ሰኔ 15/2018 በአዲስ አበባ የመማር ማስተማር ሂደቱን እያወኩ ነው የተባሉ እንደ መጠጥ ቤት እና መሰል የንግድ ቤቶችን ከመማሪያ ቤት እንዲርቁ እየተሰራ ቢሆንም ውጤቱ ግን ውሃ ቅዳ ውሃ ምልስ ሆኗል ይላል የከተማዋ ትምህርት ቢሮ፡፡ ለመጭው ትምህርት ዘመን ይህ ችግር እንዳይቀጥል ጥረቴን ቀጥያለሁም ብሏል፡፡

 
 
 
ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች?

ሰኔ 15/2018 ከአምስት አመት በኋላ በምግብ እጥረት ምክንያት የሚቀነጭሩ ህጻናት እንዳይኖሩ በሰቆጣ ቃል ኪዳን የገባችው ኢትዮጵያ እስካሁን በከወነችው ስራ ምን ውጤት አገኘች? በ2025 ስራውን በ700 ወረዳዎች ላይ ተግባራዊ አደርጋለሁ ብትልም እዛ ማድረስ ግን አልቻለችም ታዲያ ከ አምስት አመት በኋላ እንደቃሏ

 
 
 
የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡

ሰኔ 15/2018 የአሜሪካው የተራድኦ ድርጅት (USAID)ን ጨምሮ የተለያዩ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች ስራቸውን ማቋረጣቸው እና እርዳታ መቀነሳቸው እያሳደረ ያለው ጫና ከፍ ያለ መሆኑ ይነገራል፡፡ በእዚሁ ምክንያት የኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ግማሽ ያህል ሰራተኞቹን መቀነሱን እና የሰረዘው ፕሮጅክትም መኖሩን መናገ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page