በጥቂት የሰው ሃይል ስራ ከጀመሩ የግል ድርጅቶች አንዳንዶቹ ሰፍተው እና የተሻለ የስራ ዕድል ፈጥረው ውጤታማ ይሆናሉ።
- Apr 13
- 1 min read
ሚያዝያ 5/2018
በጥቂት የሰው ሃይል ስራ ከጀመሩ የግል ድርጅቶች አንዳንዶቹ ሰፍተው እና የተሻለ የስራ ዕድል ፈጥረው ውጤታማ ይሆናሉ።
ሌሎቹ ደግሞ ለስራ ማስጀመሪያ እንኳን ከተለያዩ ተቋማት የተበደሩትን ገንዘብ መክፈል አቅቷቸው ሲቸገሩ ይታያሉ።
ከ6ዓመት በፊት በሁለት የሰው ሃይል ጀምሮ ዛሬ ላይ ከመቶ በላይ ሰዎችን ቀጥሮ እያሰራ ያለ አንድ ሣሙና አምራች ድርጅት ሁሉም በኩል እየተሳካልኝ ነው ብሏል።
ዘመኑ ታከለ እና ጓደኞቹ የሣሙና ማምረት ህብረት ሽርክና ማህበር እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኝ ድርጅት ነው።
ፈሳሽ ሣሙናዎችን እንደሚያመርት የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ሃይለማሪያም ነግረውናል።
ለሰዎች ፤ ለልብስ እና ለዕቃ ማጠቢያ የሚያገለግሉ የሣሙና አይነቶችን እናመርታለን ብለውናል።
ብዙ ግብአቶችን በምርት ሂደታችን እንጠቀማለን ያሉን አቶ ዮናስ ስራው በራሱም ብዙ ኬሚካሎች ማዋሃድን የሚጠይቅ እንደሆነ ተናግረዋል። ድምጽ
ድርጅቱ በትንሽ ቦታ ላይ ስራ እንደጀመረ ያስታወሱት አቶ ዮናስ መንግስት ዕድገቱን ተከትሎ 200 ካሬ ሜትር ቦታ እንደሰጠው ነግረውናል።
አሁን በደረስንበት ዕድገት ግን ይህም ቦታ አልበቃንም ነው ያሉን።
ተጨማሪ የቦታ ጥያቄ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅርበናል ያሉን የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የማምረቻ ሼድ ማግኘት እንችል እንደሆነ በሚልም ጠይቀናል ብለዋል::
ዘመኑ ታከለ እና ጓደኞቹ የሣሙና ማምረት ህብረት ሽርክና ማህበር አሁን ላይ 103 ሰራተኞች እንዳሉት ሠምተናል።
ተጨማሪ የስራ ዕድል አሁንም እየፈጠርን ነው ሲሉም የድርጅቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ሃይለማሪያም ነግረውናል።
ድርጅቱ ከስድስት ዓመት በፊት ስራ የጀመረው በሁለት ሰው እንደነበር ሠምተናል።
ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ…..
ንጋቱ ረጋሣ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments