top of page

በኢትዮጵያ ትምህርት የቻይንኛ ቋንቋን ለማስተማር የሚያስችል የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነት መፈረሙ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ።

  • Jun 11
  • 1 min read

ሰኔ 4/2018


በኢትዮጵያ ትምህርት የቻይንኛ ቋንቋን ለማስተማር የሚያስችል የሁለትዮሽ የትብብር ስምምነት መፈረሙ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ።


ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ክንደያ ገብረሕይወት(ፕ/ር) እና በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቺን ሃይ በጋራ ፈርመውታል ተብሏል።


ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር እና በተለይም በትምህርት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር እና በባህል ልውውጥ ዙሪያ አዳዲስ ምዕራፎችን የሚከፍት ነው ብሏል ትምህርት ሚኒስቴር።



በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው ክንደያ ገብረሕይወት(ፕ/ር) ፣ ስምምነቱ ከዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ባለፈ በቱሪዝም፣ በህዝብ ለህዝብ ትስስር እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል ሲሉ አስረድተዋል።


"ዜጎቻችን የተለያዩ ቋንቋዎችን እንዲማሩ መደረጉ በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆነው እንዲወጡ ትልቅ እድል ይፈጥራል" ሲሉም አክለዋል ሚኒስትር ድኤታው፡፡


በተለይም ቻይና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂ ዘርፍ የደረሰችበትን የላቀ ደረጃ እና የነፃ የትምህርት ዕድል (Scholarship) ለኢትዮጵያውያን የምታመቻችበትን ሁኔታ ለማሳለጥ ስምምነቱ መሠረት መሆኑን አብራርተዋል።


ስምምነቱ በስርዓተ ትምህርት ዝግጅት፣ በመምህራን ስልጠና እና በቁሳቁስ አቅርቦት ላይ የቴክኒክና የቻይና ቋንቋ መምህራንን ድጋፍ የሚያጠቃልል ሲሆን፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የዕውቀት ልውውጥን እና የስኮላርሺፕ ዕድሎችንም ያሰፋል ተብሏል።


በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቺን ሃይ፤ በአሁኑ ወቅት በቻይና ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የአማርኛ ቋንቋን ማስተማር መጀመሩ የሀገራቱን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ ያጠናከረና በባህል ልውውጥ ረገድ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር በማህበራዊ የትስስር ገፁ ላይ አስፍሯል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page