top of page

በኢትዮጵያ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከአጠላቃይ ህዝቡ 17.3 በመቶው  በደም ግፊት ህመም ተጠቂ ሆኖ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

  • 15 hours ago
  • 2 min read

ግንቦት 12/2018


በኢትዮጵያ በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ከአጠላቃይ ህዝቡ 17.3 በመቶው  በደም ግፊት ህመም ተጠቂ ሆኖ መገኘቱን የጤና ሚኒስቴር ተናገረ፡፡


በዳሰሳው የማህበረሰቡ የጨው አጠቃቀም ከፍ ብሎ ታይቷል፤ ከእንቅስቃሴ የተገደበ አኗኗር እየተለመደ መምጣቱ ችግሩን እንዳያባብሰው ስጋት ፈጥሯል መባሉንም ሰምተናል፡፡


በኢትዮጵያ ከሰው ወደ ሰው የማይተላለፉ በሽታዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ማህበረሰቡን የማትቃት መጠናቸው እየጨመረ መጥቶ 50 በመቶ የሞት መንስኤዎች መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡


በሚኒስቴሩ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር ህይወት ሰለሞን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች መግቢያ በር ነው የሚባለው የደም ግፊት ህመም ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱን በቅርቡ ያደረግነው የዳሰሳ ጥናት አሳይቶናል ብለውናል፡፡


በዚህም ዳሰሳው በተሰራበት ወቅት ባለው መረጃ መሰረት ከአጠቃላይ የህዝቡ ቁጥር 17.3በመቶዎቹ የህመሙ ተጠቂ ሆነው ተገኛተዋል፤ቁጥሩ ካለፈው ዳሰሳ ጋር ሲመሳከር ከ1 በመቶ በላይ ብልጫ አለው፤የደም ግፊት ህመም የብዙ ሚሊዮኖች ችግር እየሆነ በመምጣቱ ያሳስበናል ብለውናል፡፡


የውስጥ ደዌ ሃኪም የሆኑት ዶክተር ቢኒያም ግርማ በበኩላቸው በዓለም ዙሪያ የህመሙ ተጠቂዎች ቁጥር 1.3 ቢሊዮን ጠቅሰው፤ በዚህ ጨውን አብዝቶ የመመገብ፤ የታሸጉ ምግቦችን አብዝቶ የመመገብና እንቅስቃሴ አልባ የአኗኗር ዘይቤያችን ከቀጠልን አስጊ ስለሚሆን በተለይ በመንግስት በኩል የደም ግፊት ምርመራ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲደረግ አሰራሮች መዘርጋት አለማቸው ይላሉ፡፡


ስለ ምርመራው የጠየቅናቸው በሚኒስቴሩ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚዋ ዶክተር ህይወት ሰለሞንእውነት ነው ምርመራው ቀላል መሆን አለበት ብለን፤ በመንግስት ስር ባሉ 1500 በሚሆኑ የጤና ተቋማት የደም ግፊት ምርመራን ካርድ ማውጣትና መጠበቅ ሳያስፈልግ እየሰጠን ነው፤ምርመራው በጤና መድህን ስርዓት ውስጥም ተካትቷል ሲሉም ያስረዳሉ፡፡


የዳሰሳ ጥናቱ ሌላው ያካተተው የጨው አጠቃቀምን ነው የሚሉት ዶክተር ህይወት ከገጠር እስከ ከተማ ያለልዩነት የማህበረሰቡ የጨው አጠቃቀም ከፍ ብሎ ታይቷል፤በአንፃሩ የበሽታው አጋላጭ ከሆኑት መንስኤዎች የአልኮልና የትንባሆ አጠቃቀም ላይ መቀነስ መታየቱንም ጠቅሰዋል፡፡


የደም ግፊት በሽታን ለመከላከል የተመከሩ የአኗኗር ዘይቤ ለውጦችን ከማድረግ ባለፈ በየጊዜው ግፊትን መለካት ይገባል ብለዋል ባለሙያዎቹ፡፡


በየዓመቱ ግንቦት 9 ቀን አለም አቀፍ የደም ግፊት ቀን ይከበራል፤ ዘንድሮም የደም ምርመራዎችን በማድረግ ቀኑ መከበሩን ሰምተናል፡፡

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…










Recent Posts

See All
ፋሽስት ኢጣሊያ ፣ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኙ 300 መነኮሳትና ዲያቆናት በመደዳ በጥይት ያስደበደባቸው፣ በ1929 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡

#ታሪክን_የኋሊት ፋሽስት ኢጣሊያ ፣ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኙ 300 መነኮሳትና ዲያቆናት በመደዳ በጥይት ያስደበደባቸው፣ በ1929 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ መነኮሳቱና ዲያቆናቱ እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሰጠው ጀኔራል ሮዶልፎ ግራዚያኒ ነበር፡፡ ጀኔራል ግራዚያኒ የኢጣሊያ የምስራቅ ዕዝ አዛዥና በኋላም የኢትዮጵያ የቅ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page