top of page

በምርጫ ወቅት "በታንዛኒያ እና በዩጋንዳ "ላይ የተስተዋለው የኢንተርኔት ገደብ ወይም እቀባ በኢትዮጵያ እንዳይኖር የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት ምክረ ሃሳብ ማቅረባቸውን ተናገሩ።

  • 14 hours ago
  • 2 min read

ግንቦት 12/2018


በምርጫ ወቅት "በታንዛኒያ እና በዩጋንዳ "ላይ የተስተዋለው የኢንተርኔት ገደብ ወይም እቀባ በኢትዮጵያ እንዳይኖር የአፍሪካ ህብረትን ጨምሮ ሌሎች ተቋማት ምክረ ሃሳብ ማቅረባቸውን ተናገሩ።


የአፍሪካ ህብረት ምርጫውን ለመታዘብ በቂ ዝግጅት ማድረጉን እና የምርጮ ቦርድ ውሳኔን በመጠበቅ ላይ እንደሚገኝ አስረድቷል።


ይህ የተነገረው ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ፓራዳይም ኢንሼቲቭ ከተሰኘ መንግስታዊ ካለሆነ ተቋም ጋር በመሆን በዲጂታል መብት ላይ ባሰናዳው ወይይት ላይ ነው።



በራዲሰን ብሉ (Radison blue) ሆቴል በተካሄደው ውይይቱ ላይ የአፍሪካ ህብረት፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስ የባህል ተቋም ዩኔስኮ ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ፣ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ እና የሌሎች ተቋማት እና ማህበራት ተወካዮች ተገኝተዋል።


የምርጫ ወቅት ከፍተኛ መረጃ የሚመነጭበት እና ልውውጥ የሚደረግብት ስለሆነ ለዚህ የሚያግዝ ጥራት ያለው ኢንተርኔት ተደራሽ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዳይሬክተር አቶ መሱድ ገብየሁ አሳስበዋል፡፡


ጥራት ያለው ኢንተርኔት ተደራሽ ማድረግ ምርጫው ተዓማኒ እንዲሆን ከማድረግ ባለፈ የዜጎችን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብትን መጠበቅ ጭምር መሆኑ ተጠቅሷል፡፡


አቶ መሱድ ጥራት ያለው ኢንተርኔት ከማድረስ በተጨማሪ የተዛባ እና ሃሰተኛ መረጃን ቁጥጥር የሚደረግበትን መላ መፈለግ እንደሚያስፈልግም አስረድተዋል፡፡



በተጨማሪም የኢንተርኔት መቆራረጥ "በአንዳንድ አካባቢዎች " ባለፈው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ መከሰቱን ያስታወሱት አቶ መሱድ ያለፈው ችግር በአሁኑ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ እንዳይደገም ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡


የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ የሚዲያ ክትትል ሀላፊ እና የውይይቱ ተሳታፊ ነዋል አቡበከር ጥራት ያለው ኢንተርኔት ዜጎች በምርጫ ወቅት ለሚወስኑት ውሳኔ በቂ መረጃ እንዲኖራቸው ስለሚያግዝ ጥራት ያለው ኢንተርኔት ተደራሽ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ተናግራለች፡፡


በውይይቱ ላይ ከአፍሪካ ህብረት ተወክለው የተሳተፉት አቶ ደመቀ ተስፋዬ ከ4 ወር በፊት የቅድመ ምርጫ ሂደት ትንተና ህብረቱ መስራቱን አስረድተዋል፡፡


በዚህም ቡድን ተዋቅሮ ጉዳዩ ከሚመለከተው አካል ጋርም ምርጫው ውጤታማ መሆን በሚችለብት ጉዳይ ህብረቱ መነጋገሩን ተናግረዋል፡፡



የአፍሪካ ህብረት በታዘበው የዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ምርጫ ላይ የነበረው የኢንተርኔት መጥፋት በኢትዮጵያ ላይ እንዳይከሰት ከሚመለከታቸው ጋር በቂ ንግግር ማድረጉን አቶ ደመቀ ተስፋዬ አብራርተዋል፡፡


ህብረቱ 7ኛውን አገራዊ ምርጫ ለመታዘብ ዝግጅት ማጠናቀቁንም የተናገሩት አቶ ደመቀ በሌሎች የአፍሪካ አገራት የተስተዋለው የኢንትርኔት መቆራረጥ እንዳይከሰትም ምከረ ሃሳብ ሰጥተናል ብለዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ….


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…











Recent Posts

See All
ፋሽስት ኢጣሊያ ፣ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኙ 300 መነኮሳትና ዲያቆናት በመደዳ በጥይት ያስደበደባቸው፣ በ1929 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡

#ታሪክን_የኋሊት ፋሽስት ኢጣሊያ ፣ በደብረ ሊባኖስ ገዳም የሚገኙ 300 መነኮሳትና ዲያቆናት በመደዳ በጥይት ያስደበደባቸው፣ በ1929 ዓ.ም በዛሬው ቀን ነበር፡፡ መነኮሳቱና ዲያቆናቱ እንዲገደሉ ትዕዛዝ የሰጠው ጀኔራል ሮዶልፎ ግራዚያኒ ነበር፡፡ ጀኔራል ግራዚያኒ የኢጣሊያ የምስራቅ ዕዝ አዛዥና በኋላም የኢትዮጵያ የቅ

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page