top of page

በአዲስ አበባ ከዓመታት በፊት ይታወቁ የነበሩት እነ ሜርሴዲስ ቤንዝ፣ ሬኖልት የመሳሰሉት ገበያውን ለእነ BYD ያስረከቡት በምን ምክንያት ነው?

  • sheger1021fm
  • Sep 26
  • 1 min read
ree
ree
ree

ቀድሞው በሀገር ቤት ይታወቁ የነበሩት እነ ሜርሴዲስ ቤንዝ፣ ሮልስ ሮይስ ፣ ቤንትሌይ ፣ ፎርድ፣ ካዲላክ የመሳሰሉት ቅንጡ ተሽከርካሪዎች የጎዳናው መልክ ነበሩ፡፡



በጊዜው ተሽከርካሪዎቹ የክብርም፣የአቅምም መገለጫም ሆነው አልፈዋል፡፡



አሁን ግን ያ ብዙ አይታይም፡፡



ዛሬ የከተማው መገለጫ የሆኑ በአብዛኛው የቶዮታዎቹ ላንድ ክሩዘር ፣ኮሮላ እንዲሁም በፍጥነት እያገደ የመጣው የቻይናው BYD ተሽከርካሪዎች ናቸው፡፡



በተለይ በነዳጅ የሚሰሩ የቤት ተሽከርካሪዎች መከልከልን ተከትሎ የኤዢያ በተለይም የቻይና ተሽከርካሪዎች በብዛት በጎዳናው በመታየት ላይ ናቸው፡፡



ቀድሞው በሀገር ቤት ይታወቁ የነበሩት እነ ሜርሴዲስ ቤንዝ፣ ሬኖልት የመሳሰሉት ገበያውን ለእነ BYD ያስረከቡት በምን ምክንያት ነው ስንል ከ1950ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ የአውሮፓ ተሽከርካሪዎች እና ሜርሴዲስ ቤንዝን ሬኖልት ሲያስመጣ የነበረው ኦርቢስ ኩባንያ ጠይቀነዋል።



አቶ ሳምሶን ዲምባሳ የድርጅቱ ስራ አስኪያጅ ሲሆኑ የተሽከርካሪዎቹ ተፈላጊነት አሁንም በገበያው ላይ አለ የገበያውን መልክ የተቀየረው ግን በተለይ በዋጋ ምክንያት መሆኑን ያስረዳሉ።



በኢትዮጵያ ገበያ ከ75 አመታት በላይ የሚታወቁት የአውሮፓና አሜሪካ ስሪት ተሽከርካሪዎች ዛሬም ይመረታሉ፡፡



በኤሌክትሪክ የሚሰሩም ተደርገው በየገበያው ይታያሉ፡፡ ነገር ግን በኢትዮጵያ ገበያ የአውሮፓ ስሪት የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ብዙም አይታዩም፡፡



የኦርቢስ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ሳምሶን የዚህ ምክንያት የአውሮፓዎቹ ኩባንያዎች ተሽከርካሪዎቹን እንደ ኢትዮጵያ ለመሳሰሉ ሀገራት ለመስጠት በተለይ ሃይል መሙያ (ቻርጂንግ ስቴሽን) መኖር ላይ የሚያስቀምጡት ጥብቅ መስፈርት ነው ይላሉ፡፡



ሜርሴዲስ ቤንዝና ሬኖልት የመሳሰሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ኢትዮጵያ ማስገባት ከጀመረ 75 አመታት እንደሞላው የተናገረው ኦርቢስ በአሁኑ ሰዓት በኤሌክትሪክ የሚሰሩ የአውሮፓ ምርት የሆኑ ተሽከርካሪዎች ለማምጣት ጥረት እያደረገ እንደሆነ ነግሮናል፡፡



ኦርቢስ በአሁኑ ሰዓት ለመለስኛ የጭነት አገልግሎት የሚውሉ FUSO ተሽከርካዎችና 40 ሰው ማሳፈር የሚችሉ ሜርሴዲዝ አውቶብሶችን እያስመጣ መሆኑንም ሰምተናል፡፡



ንጋቱ ሙሉ



ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page