በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 9 ወራት 83,000 ህፃናት ተወልደዋል፡፡
- 49 minutes ago
- 1 min read
ግንቦት 10/2018
በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት 9 ወራት 83,000 ህፃናት ተወልደዋል፡፡
ከሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው ዘግይተው የተመዘገቡትን ጨምሮ በአጠቃላይ ከ324 ሺህ በላይ ህፃናት ተወልደዋል ብሏል፡፡
በሌላ በኩል ኤጀንሲው በተጠቀሰው ጊዜ በከተማዋ ከ5,000 በላይ ሰዎች መሞታቸውን መዝግቤአለው ሲል ነግሮናል፡፡
የሲቪል ምዝገባና የኗሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ምዝገባዎቹን ሲያደርግ በወቅቱ በዘገየ፣ እንዲሁም የጊዜ ገደቡ ያለፈበት፣ እያለ እንደሚመዘግብ ነግሮናል፡፡

በዚህም እነዚህ 83,000 ህፃናት በተወለዱ በሰላሳ ቀን ውስጥ የተመዘገቡ እንደሆኑ እና በወቅቱ የተመዘገቡ መሆናቸውንም ኤጀንሲው አስረድቷል፡፡
ሆኖም በአጠቃላይ በ9 ወር ውስጥ ወቅቱን ጠብቀው ከተመዘገቡት ሌላ በዘገየ እና የጊዜ ገደቡ ያለፈበት ተብለው የተመዘገቡት ጋር ከ324,000 በላይ መሆናቸውንም ሰምተናል፡፡
ተቋሙ ውልደት የሚከናወንባቸው 150 ተቋማት ጋር በጋራ እየሰራ እንደሆነ የነገሩን በሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ውስጥ ምዝገባና መረጃ ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰብለወርቅ ታደሰ ናቸው፡፡
ከጋብቻ ጋር ተያይዞ በአጠቃላይ በ9 ወር በወቅቱ የተመዘገቡት 8000 መሆናቸውንም ነግረውናል፡፡
በኤጀንሲው ከተደረገ ምዝገባዎች መካከል አንዱ ፍቺ ሲሆን ወቅቱን የጠበቀ ምዝገባ ያደረጉት 3000 ናቸው ተብሏል፡፡
ይህ በወቅቱ የተደረገ የፍቺ ምዝገባ በኤጀንሲ ከፍተኛ ቁጥር ነው ሲሉ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡
ወላጆች ለልጆቻቸው በወቅቱ የልደት ሰርተፍኬት እንዲያወጡላቸው እና ለቅድመ ትምህርት ምዝገባም አስፈላጊ በመሆኑ ከወዲሁ እንዲወስዱ ኤጀንሲው ጠይቋል፡፡
ማርታ በቀለ





Comments