top of page

‘’በሌሎች ሀገራት የተውሶ ዳታ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንችልም’’ ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

  • 44 minutes ago
  • 1 min read

ግንቦት 10/2018


‘’በሌሎች ሀገራት የተውሶ ዳታ የፖሊሲ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ አንችልም’’ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።


ጠ/ሚ ዐቢይ በስታትስቲክስ የዳታ ትንተና ታግዘን ያለንን አቅም ካላወቅን ለማቀድ፣ ለመስራት፣ ለመሸጥና ለመግዛትም አስቸጋሪ ይሆናል ብለዋል።


ለዚህም የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የዳታ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ እየሰራ ያለውን ሥራ ቀለል አንድርገን የምናየው አይደለም ብለዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህንን ያሉት የፕላንና ልማት ሚንስትር ከኢትዮጵያ ስታስትስቲክ አገልግሎት ጋር በመሆን "የዳታ ሉዓላዊነት ለፖሊሲ ነፃነት" በሚል መሪ ቃል ባዘጋጁት የብሔራዊ ጉባኤ እና ኤግዚቢሽን የመክፈቻ መድረክ ላይ ነው።


የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት በዚህ ዓመት ከ80,000 በላይ ዳታ ሰብሳቢ ሰራተኞችን ወደ 19,600 ቀበሌዎች በማሰማራት በሥነ ህዝብና ጤና፣ በግብርና፣ በተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት እና የቢዝነስ ተቋማት ቆጠራ ሲያካሂዱ እንደነበር ተነግሯል።

ይህም "በዳታ ሉዓላዊነት የማስጠበቅ አንዱ ሂደትና የሚያኮራ ሥራ ነው" ሲሉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አወድሰውታል።


የመረጃ ወይም ዳታ ስብሰባው፣ የትንተና እና የማረጋገጥ ሂደቱ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የተሰራ ነው ተብሏል።


ይህም ኢትዮጵያ በዳታ ሉዓላዊነቷን የማስጠበቅ ጉዞ ላይ ስለመሆኑ እንደ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።


ፕላንና ልማት ሚንስትር ከኢትዮጵያ አገልግሎት ጋር በመሆን ባዘጋጁት "የዳታ ሉዓላዊነት ለፖሊስ ነፃነት" ብሔራዊ ጉባኤና ኤግዚቢሽን ላይ ጠ/ሚ ዐቢይን ጨምሮ ሚንስቴሮች፣ ሚኒስቴር ዴኤታዎች፣ አምባሳደሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


ዛሬ ግንቦት 10 የተከፈተው ኤግዚብሽን እስከ እስከ ረቡዕ ግንቦት 12 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ይቆያል ተብሏል።


ንጋት መኮንን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page