በ"ፊንቴክ ኢንቨስትመንት" ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ ዓቃቢ ህግ ክስ እንዲመሰርት 7 ቀናት ተፈቀደለት፡፡
- 6 minutes ago
- 1 min read
ሚያዝያ 21/2018
በ"ፊንቴክ ኢንቨስትመንት" ማጭበርበር የተጠረጠሩ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮች ላይ ዓቃቢ ህግ ክስ እንዲመሰርት 7 ቀናት ተፈቀደለት፡፡
በፊንቴክ ኢንቨስትመንትሽፋን በተፈጸመ የማጭበርበር ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉ አርቲስቶች እና ቲክቶከሮችን ጉዳይ ለመመልከት የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ለ ዓቃቢ ህግ ክስ መመስረቻ 7 ቀን የፈቀደው፡፡
ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረው ፖሊስ የምርመራ ስራዎችን አጠናቆ አንዲያቀርብ ነበር፡፡
በዛሬው ችሎትም ፖሊስ ምርመራውን መጨረሱንና ጉዳዩን ለዓቃቢ ህግ ማስተላለፉን አስረድቷል፡፡
ዓቃቢ ህግም ክስ ለመመስራት ፍርድ ቤቱን 10 ቀናት ጥይቆ 7 ቀናት ተፈቅዶለታል፡፡
በዚህም ለሚያዚያ 28/2018 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
የፊንቴክ ኢንቨስትመንት ድርጅትን ባልተገባና በተጋነነ መልኩ በማስተዋወቅ በህገወጥ መንገድ ከተሰበሰበው ገንዘብ ተጋሪ በመሆን የተጠረጠሩ ሰለሞን ቦጋለ፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ዳንኤል ተገኝ፣ አብርሃም ግዛው፣ ይገረም ደጀኔ፣ መንሱር ጀማል እና ካሊድ ናስር የተባሉ ታዋቂ አርቲስቶችና የማስታወቂያ ባለሙያዎችንም የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር ካዋላቸው አንድ ወር ሆኗቸዋል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Website፡ https://www.shegerfm.com/
YouTube : https://shorturl.at/18TS1
Telegram : https://shorturl.at/68aeK
Facebook፡ https://shorturl.at/tm5Q4
WhatsApp : https://shorturl.at/8vwRx
X :- https://x.com/shegerfm?s=2
LinkedIn: https://shorturl.at/Vfe6i
Tiktok : https://shorturl.at/lhYiv
Instagram: https://shorturl.at/9X4S7





Comments