top of page

ሰኔ 9 2017 - በጉዲፈቻ ልጅ ለሚያሳድጉ ወላጆች የወሊድ ፈቃድ መብት እንደሚሰጣቸው ስለ እናት በጎ አድራጎት ድርጅት ጠየቀ

  • sheger1021fm
  • 21 hours ago
  • 1 min read

ድርጅቱ ይህንን ጥያቄ ያቀረበው በዛሬው እለት ታስቦ የሚውለውን የአፍሪካ የህፃናት ቀንን አስመልክቶ በትናንትናው እለት በካሄደው ፕሮግራም ነው።


ስለ እናት በጎ አድራጎት ድርጅት ላለፉት 23 ዓመታት በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች እና አሁን ላይ ደግሞ በአዲስ አበባ እና ሻሸመኔ ከተማ ላይ ወላጆቻቸውን በተለያዩ ምክንያት ላጡ ህጻናት እና አቅመ ደካማ ቤተሰቦች እየደገፈ እንደሚገኝ ስራ አስኪያጁ አቶ ያሬድ አብዱ አስረድተዋል።


በ23 ዓመታት ውስጥም ከ4,500 በላይ ድርጅቱ መደገፉን ተናግሮ በአሁኑ ሰዓትም ደግሞ በአጠቃላይ 1,700 ህፃናት በተለያየ መንገድ እየደገፈ እንደሆነ ተጠቅሷል።


ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት ረጂና አሳዳጊ የሌላቸውን ህፃናት እንዲንከባከብ ብዙ ጥያቄ እንደሚቀርብለት ተናግሮ ይሁን እንጂ በአቅም ውስንነት የተነሳ የሚቀርብለት ጥያቄ በሙሉ ለመቀበል እንደሚቸገር አቶ ያሬድ ጠቅሰዋል።


የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ እንደ ስለእናት በጎ አድራጎት ድርጅት ያሉ በህፃናት ማሳደግና እንክብካቤ ላይ የሚሰሩ 109 ድርጅቶች እንዳሉ ነግሮናል።


ህፃናትን ከጎዳና እያነሱ ወደ ቤተሰቦቻቸው መቀላቀል ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ሆኗል ያለው ሚኒስቴር መ/ቤቱ ህፃናት ቀድሞውንም ወደ ጎዳና እንዳይወጡ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራሁ ነው ብሏል።


ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page