ሰኔ 30 2017 - የተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ
- sheger1021fm
- Jul 7
- 1 min read
የኢትዮጵያ ግብርናን ከኬሚካል ማዳበሪያ ያላቅቃሉ የተባሉ የፈጠራ ሃሳቦች፤ በተለያዩ ጊዜያት ተሰሩ ተብሎ ሲነገሩ ሰምተናል፡፡
እነዚህ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎች የአፈር አሲዳማነትን ከመከላከልም ባለፈ ምርትና ምርታማነትን እንደሚያሳድጉም ይነገራል፡፡
በቅርቡ በተደረገው አዩቴ አፍሪካ ቻሌንጅ ኢትዮጵያ 2025 የስራ ፈጠራ ውድድር ላይ ከቀረቡና ውድድሩ ላይ አሸናፊ ከሆኑ ስራዎች መካከል የተፈጥሮ #የአፈር_ማዳበሪያ ዋነኛው ነው፡፡
አማረ አዲስ የናኔክስ ሾልሽን መስራችና በተፈጥሮ አፈር ማዳበር የውድድሩ አንዱ አሸናፊ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ ቀደም ባለው ጊዜ ያለው ግብርና ስራ ይቀላጠፍ የነበረው በተፈጥሮ የአፈር ማዳበሪያ ነው፡፡
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በኬሚካል ማዳበሪያ ተቀይሯል ይላሉ፡፡
አሁን በቴክኖሎጂ በታገዘ መንገድ የተፈጥሮ ማዳበሪያን ማምረት እንችላለን ይህም በሙከራ አረጋግጫለሁ በማለት ያስረዳሉ፡፡

ሌላው የውድድሩ አሸናፊ ዶክተር ባምላክ ካሳሁን ተፈጥሯዊ የአፈር ማዳበር የእስሳት መኖና ለባዮ ጋዝ የሚያገለግል የፈጠራ ስራን ሰርተዋል፡፡
ምርቱም ሙከራ ተደርጎለት ውጤታማ መሆኑን አይተናል ሲሉ ያስረዳሉ፡፡
አቶ አማረ አዲስ አሁን የኬሚካል ማዳበሪያ ዋጋ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል ይህ ደግሞ በምርቶች ዋጋ ጭማሪ እንዲኖር እያደረገ መሆኑን ያስረዳሉ፡፡
የኬሚካል ማዳበሪን ለማስቀረት በማሰብ የአፈር ማዳበሪያ የፈጠራ ስራ የሰሩት ሁለቱም ባለሙያዎች ፋይናንስ ችግር ከተቀረፈልንና የምናለማበት ቦታ መንግስት ካመቻቸልን ምርታችንን በፍጥነት ለገበሬው አምርቶ ለማቅረብ እኛ ተዘጋጅተናል በማለት ነግረውናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
በረከት አካሉ











Comments