top of page

ሰኔ 30 2017 - የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ ላይ እየተደረገ ያለው ማሻሻያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ወደ ቀድሞው ማነቆ ሊመልሳቸው ነው የሚል ስጋት ፈጥሯል

  • sheger1021fm
  • Jul 7
  • 1 min read

የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች አዋጅ በስድስት ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ተሻሽሏል፡፡


ቀድሞ የነበረው ህግ ከሚያገኙት የገንዘብ ድጋፍ ከ10 በመቶ በላይ ከሃገርና ከውጭ ካሉ የገንዘብ ምንጮች የሚያገኙ ከሆነ በፖለቲካና መብት ጉዳይ ላይ እንዳይሰሩ ይከለክል ነበር፡፡


የተጠቀሰው እና ሌሎችም የሲቪል ማህበራትን አላሰራ ያሉ አንቀፆች ተሻሽለው ከ6 ዓመት በፊት አዋጁ ፀድቆ ነበር፡፡


አሁን በአዋጁ ላይ እንደገና እየተደረገ ያለው ማሻሻያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶችን ወደ ቀድሞው ማነቆ ሊመልሳቸው ነው የሚል ስጋት ፈጥሯል፡፡


አዲሱ የህግ ማሻሻያ በምርጫ ጉዳይ ማህበረሰብን ለማንቃትና መሰል ስራዎች ለመስራት የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከናካቴው ከውጭ ገንዘብ መቀበል አይችሉም ይላል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/586/

ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page