top of page

ሰኔ 27 2017 - የአለም ባንክ ለኢትዮጵያ 1 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ እና ብድር ለመስጠት ተስማማ

  • sheger1021fm
  • Jul 4
  • 1 min read

የአለም ባንክ የ1 ቢሊዮን የፋይናንስ ስምምነትን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እና የአለም ባንክ የኢትዮጵያ የኤርትራ፣ የሱዳን እና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ማሪያም ሳሊም ፈርመውታል፡፡፡


በአንድ ቢሊዮን ዶላሩ ምን ያህሉ በድጋፍ እና ምን ያህሉ ደግሞ በረጅም ጊዜ የሚመለስ ብድር እንደሆነ በገንዘብ ሚኒስቴር መግለጫ ላይ አልተጠየቀም፡፡

ree

ገንዘቡ የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እና አካታች እድገትን ለማገዝ ይውላል ተብሏል፡፡


የፋይናንስ ዘርፉን ለማረጋጋት፣ የንግድ ተወዳዳሪነትን ለማበርታት፣ የሀገር ውስጥ የሀብት አሰባሰብን ለማጠናከር፣ ግልፅ እና ውጤታማ የመንግስት አስተዳደርን ለማሳደግ እንዲሁም ማህበራዊ አገልግሎቶችን በዘላቂነት ማረጋገጥ በአንድ ቢሊዮን ዶላር የሚሰሩ ስራዎች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡


ስምምነቱ የአለም ባንክ የኢትዮጵያ የሪፎርም አጀንዳ ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል የተባለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት የአለም ባንክ ማመስገኑ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page