ሰኔ 21 2017 - የማዳበርያ ግዢ ስርዓትን ያዘምናል ተብሎ እየለማ ያለው መተግበርያ በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ይፈታል ተብሎ ተስፋ እንደተጣለበት ተነገረ
- sheger1021fm
- 17 minutes ago
- 1 min read
መተግበሪያው ከወደብ አንስቶ እስከ ቀበሌ ድረስ የማዳበርያ ሂደትን መከታተል እንደሚቻል ተነግሯል።
ወደ ሃገር ቤት የሚገባው ማዳበርያ ወደ ክልሎች ከተላከ በኋላ ከስርጭትና ከክፍያ ጋር በተያያዘ ችግሮች እንዳሉ የተነገረ ሲሆን እየለማ ያለው መተግበርያ ይህን ክፍተት ይሞላል ተብሏል።
የማዳበሪያ ስርጭት ከተደረገ በኋላ በህገወጥ መንገድ ግዢዎች ሲደረጉ ይታያል ይሁን ማስተካከል የሚቻለው በቴክኖሎጂ ሲታገዝ መሆኑንም ሰምተናል።

የኢትዮጵያ ገበሬ ከቴክኖሎጂ ጋር ያለው ቅርበት ይታወቃል የሚለማው መተግበርያ ይህንን ታሳቢ ያድርግ ሲባልም ተጠይቋል፡፡
መተግበርያው የማዳበያ ፍላጎትን ከተጠቃሚው ለመሰብሰብ፣ ማዳበርያው ወደ ሃገር ቤት ከገባ በኋላ የት ደረሰ የሚለውን ለመከታተልና በግዢ ወቅት በቀላሉ ክፍያ መፈፀም ያስችላል ተብሏል።
መተግበሪያውን የግብርና ሚንስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን እየለማ መሆኑን ሰምተናል።
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://shorturl.at/P4mpX
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios