top of page

ሰኔ 2 2017 - የባህል ህክምና በኢትዮጵያ ረዥም ታሪክ ማስቆጠሩ ቢነገርም በዘመናዊ መንገድ መድሃኒት ለማምረትና ከሳይንሱ ጋር መሳ ለመሳ የመሄዱ ነገር አይታይም፡፡

  • sheger1021fm
  • 8 minutes ago
  • 1 min read


የጉሌ እፅዋት ማዕከል ይህን ለማስቀረት ከባህል ሐኪሞች ጋር በጋራ እየሰራሁ ነው ብሏል፡፡

ሊጠፋ የተቃረቡ እፅዋትን ሰጥተውኝ አባዝቼ ልሰጣቸውም ተስማምቻለሁ ይላል፡፡


በሀገሪቱ ያሉ በርካታ እፅዋቶች የመጥፋት አደጋ እንዳንዣበበባቸውም ማዕከሉ ተናግሯል።


የጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል የምርምርና ልማት ዳይሬክተር ዶ/ር ብርሃኑ በላይ ዕፅዋቶች ለህክምናው ዘርፍ የማይተካ ሚና ስላላቸው የባህል መድሀኒት አዋቂዎችን ከዘመናዊ ህክምናው ጋር እንዲሰሩ አስቻይ ሁኔታዎችን እየፈጠርን ነው ሲሉ ተናግረዋል።


ማዕከሉ ዕፅዋቶች የመጥፋት አደጋ እንዳይገጥማቸው በሰፊው እየሰራ ቢሆንም የውሃ አቅርቦት በዘርፉ የተማረ የሰው ሀይል አለመኖር እና መሰል ችግሮች ስራቸውን በሚገባ እንዳይከውኑ እንቅፋት እንደሆነባቸውም ነግረውናል።


ከዚህ ቀደም በሀገሪቱ ያሉ ዕፅዋቶች የመጥፋት አደጋ ተጋርጦባቸው ዳግም እንዲያንሰራሩ የተደረገበት ሁኔታ እንደነበር ያስታወሱት ዶ/ር ብርሃኑ አሁንም ቢሆን በርካታ የመጥፋት አደጋ አዛቦባቸዋል ብለዋል።


ይህ እንዲሆን ካደረጉት ምክንያቶች እርሻን ለማስፋፋት ሲባል የሚደረግ ደን ማቃጠል አንዱ እንደሆነም ይናገራሉ።


ፍቅሩ አምባቸው


コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page