top of page

ሰኔ 12 2017 - በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት ከ10,000 በላይ ሴቶች ያስገድዶ መደፈር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ጥናቶች ያሳያሉ

  • sheger1021fm
  • 9 minutes ago
  • 1 min read

በትግራይ ክልል በነበረው ጦርነት ምክንያት ከ10,000 በላይ ሴቶች ያስገድዶ መደፈር ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ጥናቶች ያሳያሉ፡፡


ይህ ችግርም ጠባሳ ጥሎ እንዳያልፍ ሊከወኑ ስለሚገቡ ጉዳዮች ባለሞያዎች መክረዋል፡፡


በክልሉ ሰላም ቢሰፍንም በሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች ግን አሁንም ድረስ መቀጠላቸው ደግሞ ችግሩን ያባብሰዋል ተብሏል፡፡


በክልሉ ያለው የፈትህ ሥርዓት ወደ ነበረበት አለመመለሱ፣ የጤና ተቋማት ሙሉ በሙሉ ስራቸውን መከወን ባለመጀመራቸው እና በሌሎችም ችግሮች ምክንያት የሴቶች ጥቃት ሊቀጥል መቻሉን ጥናቶችን ጠቅሰው የነገሩን በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መምህርና የማህበረሰብ ሳይንስ አጥኝ የሆኑት አቶ ዘርዓብሩክ ዘውዱ ናቸው፡፡


የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ወደ ስራ አለመግባታቸው ሴቶቹ ጥቃት ሲደርስባቸው ወዴት ሄደው አቤት ማለት እንዳለባቸው ይቸገራሉ የተባለ ሲሆን መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችም ቢሆኑ ተደራሽነታቸው ውስን ነው ተብሏል፡፡


ሙሉ ዘገባውን በድምጽ ያድምጡ…. https://www.mixcloud.com/ShegerFM/fyujye5656756/

ፋሲካ ሙሉወርቅ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page