top of page

ሰኔ 11 2017 - የአባይ ተፋሰስ ሀገራትን በኤሌክትሪክ ኃይል ለማስተሳሰር ከተናጠል ውይይት ይልቅ ራሱን ችሎ የሚሰራ ቀጠናዊ ተቋም ቢመሰረት ይበጃል የሚል ሀሳብ ቀረበ

  • sheger1021fm
  • 4 hours ago
  • 1 min read

እንዲህ ዓይነቱ ተቋም መመስረቱ አባል ሀገራት ያለባቸውን የፖሊሲ እና ሌላውንም የአሰራር ችግር አናበው መስራት እንዲችሉ ያግዛችዋል የተሻለ ትብብርም በቀጠናው ይፈጥራል ተብሏል፡፡


የአባይ ተፋሰስ ሀገራት የውሃ ሃብቱን በትብብር ማልማት እና መጠቀም በሚችሉበት ሀሳብ ዙሪያ የሚመክረው የአፍሪ ራን አራተኛው ጉባኤ ትናንት በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡


የቀጠናውን ሀገራት በኤሌክትሪክ መስመር ማስተሳሰር የዘንድሮ መነጋገሪያ ሀሳብ ነበር፤ ዶክተር ግዛቸው አስራት በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ጉዳዮች ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር ጄነራል ናቸው፡፡


እሳቸው እንደሚሉት የቀጠናው ሀገራት በተለያየ መንገድ ኃይል ሊያመርቱ የሚችሉበት አቅም ቢኖራቸውም አንዱ ሃገር ግን ከሌላው ጋር የተሳሰረ አይደለም ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት የኤሌክትሪክ ሃይልን ለኬንያ ሱዳን እና ጅቡቲ እየሸጠች ነው፤ ደቡብ ሱዳን ሶማሊያና ታንዛኒያም በቅርቡ ተጨማሪ የኃይል ገዢ ሀገሮች ይሆናሉ ተብሏል፡፡


ዳርእስከዳር ታዬ(ዶ/ር) በውጭ ጉዳይ ኢንስትቲዩት መሪ ተመራማሪ ናቸው እሳቸው እስካሁን ያለው የሃይል ሽያጭ በሁለትዮሽ ስምምነት እንደሚፈፀም አንስተው ከዛ ይልቅ ግን በቀጠናው ባለቤት ሆኖ የሚሰራ ራሱን የቻለ ተቋም ቢመሰረት የሚል ሀሳብ መነሳት እየጀመረ እንደሆነ ነግረውናል፡፡


ባለሙያው በተለያዩ የመሰረተ ልማት ትብብሮች ላይ በተናጠል ከመነጋገር ራሱን የቻለ ተቋም ወደ ማቋቋም መሸጋገር በሂደት እውነተኛ የኢኮኖሚ እና ሌላውንም ውህደት እያመጣ መሄዱ አይቀርምም ብለዋል፡፡


የህዳሴው ግድብ ከፍጻሜው መቃረቡን ተከትሎ አሁን በኢትዮጵያ በኩል የተመረተውን ኃይል ኢትዮጵያም የአካባቢው ሀገራትም እንዴት ይጠቀሙ የሚል አይነት ሃሳብ ወደፊት እየመጣ ስለመሆኑም ነግረውናል፡፡


ትናንት የተካሄደው የአፍሪ ራን ጉባኤ በየዓመቱ በአባይ ተፋሰስ ሀገራት የጋራ ጉዳዮች ዙሪያ ሀሳብ እየመረጡ በጥናት የተደገፈ ውይይት የሚደረግበት መሆኑን ሰምተናል፡፡


በትናንቱ ጉባኤ ላይ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ሲናገሩ እንደሰማነው ኢትዮጵያ እስከ 60,000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨት የሚያስችል አቅም አላት ከዛ ውስጥ እስካሁን መጠቀም የቻለችው 10 በ1መቶውን ብቻ ነው ብለዋል፡፡


ቴዎድሮስ ወርቁ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…





Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page