ሰኔ 10 2017 - ኢትዮ ቴሌኮም ከፋይናንስ እና ሌሎች ዘርፍ ባለፈ የዘረጋሁትን መሰረተ ልማት በመጠቀም የግብርናውን መንገድ በቴክኖሎጂ ለማሰልጠን መንገድ ጀምሬያለሁ አለ።
- sheger1021fm
- 10 hours ago
- 2 min read
ኢትዮ ቴሌኮም ከፋይናንስ እና ሌሎች ዘርፍ ባለፈ የዘረጋሁትን መሰረተ ልማት በመጠቀም የግብርናውን መንገድ በቴክኖሎጂ ለማሰልጠን መንገድ ጀምሬያለሁ አለ።
ገበሬው፤ ቆፍሮ ነዋሪው የሀገር ሰው፤ ምርቱ እንዲንበሸበሽ ልፋቱና ድካሙ እንዲስማማለት፤ በመረጃ እና በቴክኖሎጂ የታገዘ፤ በሳተላይት እና በሌሎችም ቴክኖሎጂ የተደገፈ እርሻ እንዲስፋፋ ወደ ስራ መገባቱ ተሰምቷል።
ኢትዮ ቴሌኮም በ ኢትዮዽያ የአፈር እርጠበት መጠንን የሚለይ እንዲሁ ለገበሬውና ለሚያመርተው ተያያዥ የንግድ ሰንሰለት የዲጅታል መፍትሄ ማቅረቡን ተናግሯል።
ኩባንያው አቀረብኩ ያለው የዲጅታል መፍትሄ በ ቆላ ደጋው እንዲሁም በመላው ኢትዮዽያ በመልክአ ምድር ለግብርናው ተሰማሚ እንደሆነ አስረድቷል።

ገበሬው በ እርጥብ መሬት ሁሉ የሚዘራው እንደተፈለገው ስለማይበቅልለት፤ በየት ቦታ ምን ይዘራ ማዳበሪያውስ ምን አይነት መሬት ይፈልጋል በሚለው ዙሪያ የዲጅታል መፍትሄው መላ ይዟል ተብሏል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የግብርናው ዘርፍ በቴክኖሎጂ ስንፍና ምክንያት ጉልበቱ እንዳይታጠፍ በብርቱ እየደከምን ነው ብለዋል።
ሌት ተቀን ለሚለፋት ገበሬዎች በቴክኖሎጂ አግዞ በፋይናንስ እረድቶ የምግብ ጥራት እና ብዛት ለማሻሻል ኩባንያው መንገድ መጀመሩን ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አስረድተዋል።
ይህ በተለይ ለኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የቀረበው የዲጅታል መፍትሄ ከፍተኛ ጥናት እና ምርምር እንደተደረገበት ፍሬህይወት ታምሩ አስረድተዋል።
ኩባንያው ቴክኖሎጂን ከመታጠቅ ባለፈ በብዙ ዘርፍ ውስጥ እያስገባሁ ለውጥ እያየሁበት ነው ፤ ውጤቱንም እየቆጠርኩበት ነው ብሏል።
ዛሬም ከፋይናንስ ዘርፍ ባለፈ ቴክኖሎጂ ውን በመጠቀም ግብርናውን ለማሰልጠን መንገድ መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስረድቷል።
ምን ያህል ምርት ተመረተ? ገበሬው ለፍቶ ያመረተው እንዴት ወደገበያው ይድረስ ሰንሰለቱንስ እንዴት ያመቻች ? በየትኛው መሬት ምን ይመረት? የአየር ጠባዩ ለየትኛው ምርት የተመቸ ነው የሚለውን እና ሌላውንም የግብርና ስራ ቀላል እነወደሚያደርገው የ ኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ኢንተርፕራይዝ ሶሉሽን አኦፊሰር አቶ ዮሐንስ ጌታሁን ተናግረዋል።
የ ኦሮሚያ ክልል የግብርና ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌቱ ገመቹ በበኩላቸው ይህ መፍትሄ የግብርና ባለሙያዎች የተሻለ መረጃ እንዲኖራቸው ፤ ገበሬው በድካሙ ልክ እንዲጠቀም መንግስትም በተለያዩ መረጃዎች እየታገዘ እና መረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲወስን ያግዘዋል ብለዋል።
ኢትዮ ቴሌኮምና የኦሮሚያ ግብርና ቢሮ በዚሁ ጉዳይ አብሮ ለመስራት ዛሬ ውል ቋጥረዋል።
ተህቦ ንጉሴ
Comments