top of page

ሚያዝያ 29 2017 - ‘’ቀን ከለሊት ዋጋ የሚከፍሉ የፀጥታ አካላት እንዳሉ ሁሉ፤ በህግ ላይ የሚያምጹ የፀጥታ አካላትም አሉ’’ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ

  • sheger1021fm
  • 2 days ago
  • 1 min read

የፌዴራል መንግስት የማያውቃቸው በክልሎች የሚተዳደሩ 297 ኬላዎች መኖራቸው ተነገረ፡፡


ኬላዎቹ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጭምር እንዲነሱ የተወሰኑ፤ ነገር ግን እስከአሁን ያልተነሱ በክልሎች የሚተዳደሩ መሆናቸው ተነግሯል፡፡


ይህ የተነገረው የገቢዎች ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት ለህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት የ9 ወራት የስራ ክንውን ሪፖርቱን ባቀረበበት ወቅት ነው፡፡


በምክር ቤቱ የፕላን በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በክልሎች እንዲነሱ የተወሰኑ ኬላዎች ባለመነሳታቸው በገቢ እና ወጪ ንግዶች ላይ እንዲሁም በሸቀጦች ነፃ ዝውውር ላይ አሉታዊ ጫና እያሳደሩ እንደሆነ ማረጋገጡን ተናግሮ ለምን ኬላዎች እንዳልተነሱ ጠይቋል፡፡


የጉሙሩክ ኮሚሽን በበኩሉ ‘’ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌዴራል ፖሊስ እና ሌሎች የጸጥታ አካላት በተገኙበት በተደጋጋሚ አቅጣጫ ቢስጡበትም ችግሩ ቀጥሏል’’ ብሏል፡፡


በፓርቲ ጉባኤዎች ላይ እና በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጭምር በክልሎች ያሉ የፌደራል መንግስት የማያውቃቸው ኬላዎች እንዲነሱ መመርያ ቢተላለፍም በቅርቡ የፀጥታ ችግር በሌለባቸው አካባቢዎች ላይ በተደረገ ጥናት 297 ኬላዎች መኖራቸውን አረጋግጠናል ሲሉ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ ተናግረዋል፡፡


በህገ ወጥ ኬላዎች ምክንያት ዜጎች እየተንገላቱ መሆኑንን የተናገሩት ኮሚሽነሩ የተከበረውን ምክር ቤት እርዳታ እንሻለን ብለዋል፡፡

ቀን ከለሊት ዋጋ የሚከፍሉ የፀጥታ አካላት እንዳሉ የተናገሩት ኮሚሽነሩ፤ በህግ ላይ የሚያምጹ የፀጥታ አካላት እንዳሉም በምክር ቤት ቆይታቸው ጠቁመዋል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…..


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page