ሚያዝያ 20 2017 - ተደረገ የተባለው ለውጥ ከወዲሁ ምን አመላካች ያሳያል?
- sheger1021fm
- Apr 28
- 1 min read
ኢትዮዽያ የሚበጀውን ኢኮኖሚ ልከተል፤ በተደጋጋሚ ተበላሽቶ የነበረውን የፋይናንስ የኢኮኖሚ ስርዓት፣ ወግ ላስይዝ ብላ አዲስ መንገድ አንጥፋለች።
ይህንኑ ስራ በተመለከተ ለውጡን አሁን አትጠብቁ፣ ታገሱ መንግስትን ጠብቁ ሲሉ የአለም የገንዘብ ድርጅት እና ሌሎችም እኛ እናውቅላችኃለን የሚሉት እርዳታ ሰጭዎች ይናገራሉ ያስረዳሉ።
የሆነው ሆኖ ለውጡና ኑሮው ያልተገናኘለት ህዝብ ውጤቱን ጠብቅ ፤ ታገስ ሲባል ምን ማለት ነው?
ይህ ተደረገ የተባለው ለውጥ ከወዲሁ ምን አመላካች ያሳያል።
አብዱልመናን ሙሀመድ(ዶ/ር) በፋይናንስ እና አካውንቲንግ እረዘም ያለ ልምድ አላቸው።
እሳቸው በዚሁ ሙያ በእንግሊዝ እና በኢትዮዽያ 25 ዓመት ልምድ አላቸው።
ዶር አብዱልመናን የአይ ኤም ኤፍን ሐሳብ እና የውጭ ምንዛሪ ድልድሉን እንዴት ይተነትኑታል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Telegram; https://t.me/ShegerFMRadio102_1
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comentarios