top of page

ሚያዝያ 20 2017 - በኢ - መደበኛ ኢኮኖሚ ወጭዎችን በተለየ የውጭ ምንዛሪ ማዳን

  • sheger1021fm
  • Apr 28
  • 1 min read

ምጣኔ ሐብት


በየቦታው ሥራ አለ፣ ቢዝነስ አለ።


አስናቀ በእጅ ሞያ የ25 ዓመት ልምድ አለው።


ቀላል ግጭት ያጋጠማቸውን ተሽከርካሪዎች፤ እሱ ባለው የእጅ ሞያ የተሰበረ እስፖኪዮ፣ የኋላ እና የፊት መብራት፣ ፍሬቻዎች፣ የመኪና አካል ግጭት እጠግናለሁ፤ እንደነበረ ቁጭ አደርገዋለሁ ይላል።


ደንበኞቹ ብዙ እንደሆኑ ነግሮናል።


በአስናቀ ሥራ ቦታ የማይመጡ ተሽከርካሪዎች የሉም።


ከትልልቅ ቪ-ኤት ተሽከርካሪዎች ጀምሮ እስከዘመኑ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች በእጁ ሞያ ይጠግናቸዋል።


አስናቀ አሚዴ ይህን የለመድኩት እጄን እየተኮስኮ እና እየተጎዳሁ ነው ብሏል።


ለዚህ ሞያ የጋሉ ቢላዎች፣ ማንደጃ እና የተለያዩ ቀላጮችን እንደ ግብዓት ይጠቀማል።


በዚህ ኢ - መደበኛ ኢኮኖሚ ወጭዎችን በተለየ የውጭ ምንዛሪ እያዳነ እንደሆነ አስናቀ ይናገራል።


በዛሬው የምጣኔ ሐብት ዝግጅት አስናቀ አሚዴ እንግዳችን ነው።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….



ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…






コメント


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page